Page 1 of 1

ተአምረኛው የክርስቶስ የመስቀል ላይ ስዕል በሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ

Posted: Mon Apr 21, 2025 9:17 pm
by dan

ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ስእል በሚያስተምርበት ወቅት ተማሪዎቹ የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ስለው እንዲያመጡ በቤት ሥራ መልክ አዘዛቸው። ሁሉም በመሰለው መልክ ክርስቶስን ስሎ ሲያመጣ አንድ ተማሪ ግን የክርስቶስን ሥዕል በጥቁር ወይም አፍሪካዊ መልክ ስሎ ያስረክባል። ገብረ ክርስቶስ በስዕሉ ተገርሞ ለምን ክርስቶስን ጥቁር አድርጎ እንደሳለው ሲጠይቀው "ክርስቶስ ፈረንጅ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ፈረንጆች በጣም ጨካኞች ናቸው። ኢየሱስ ክርስቶስም ነጭ ሳይሆን ጥቁር ነው!" ብሎ ይመልሳል።
ይህን ግዜ ነው ገብሬ ወደቤቱ ሲበር ሄዶ የዓለም መድኀኒት ኢየሱስ ክርስቶስን ቀለም እንዳይኖረው ፣ ዘር እንዳይኖረው ፣ ነገድ እንዳይኖረው አርጎ ከፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ በደም ለውሶ ሣለው።

ከመከመፅሐፍት አለም (ከማህበራዊ ሚድያ)

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ!

eastern.jpeg
eastern.jpeg (148.51 KiB) Viewed 10998 times