በሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ የጂሃድ ጥሪ አወጁ?
በሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ የጅሃድ ጦርነት እንዲታወጅ ጥሪ ቀረበ። የሶማሊያ ወጣቶች መንግስታቸው ከአልሸባብ ጋር ተባብሮ እንዲሰራ ጠይቀዋል። የሚሉ ዜናዎች እየተሰሙ ነው። እውነት ነወይ? ከሆነ ምን ማለት ነው? የጅሃድ ጥሪያቸውን ማነው የሚመልሰው?
በሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ የጅሃድ ጦርነት እንዲታወጅ ጥሪ ቀረበ። የሶማሊያ ወጣቶች መንግስታቸው ከአልሸባብ ጋር ተባብሮ እንዲሰራ ጠይቀዋል። የሚሉ ዜናዎች እየተሰሙ ነው። እውነት ነወይ? ከሆነ ምን ማለት ነው? የጅሃድ ጥሪያቸውን ማነው የሚመልሰው?
የጅሃድ ጥሪ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ከሽፏል። የማይሆን ምኞት ነው። ሁለቱም አገራት ችግራቸውን በንግግር እንደሚፈቱ እገምታለሁ። ለጦርነት የሚሆን ጉልበት የላቸውም አጉል መወራጨት ካልሆነ በስተቀር።
ውድ ዳን መችና በየትኛው የመገናኛ ብዙሃን ይህ ጥሪ እንደተላለፈ መረጃው ካሎት ሊያካፍሉን ይችላሉ? የዜናዎ ምንጭ ማን ነው?
dan wrote: Mon Jan 08, 2024 4:24 amበሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ የጅሃድ ጦርነት እንዲታወጅ ጥሪ ቀረበ። የሶማሊያ ወጣቶች መንግስታቸው ከአልሸባብ ጋር ተባብሮ እንዲሰራ ጠይቀዋል። የሚሉ ዜናዎች እየተሰሙ ነው። እውነት ነወይ? ከሆነ ምን ማለት ነው? የጅሃድ ጥሪያቸውን ማነው የሚመልሰው?
በማሕበራዊ ሚድያ ሲዘዋወር ነው የሰማሁት። ቋንቋውን ስለማልሰማ ትክክለኛው ምንጭ ማቅረብ አልችልም። የኔ ጥያቄ በመንግስታዊ የሚድያ አውታሮች ጥሪው ቢተላለፍስ በአገራችን የሚያስከትለው ነገር ይኖራል ዎይ? ከሀይማኖት መሪዎች ምን ይጠበቃል? ለማለት ነው።
ሠላም የዚህ ፎረም ተሳታፊዎች
አቶ ዳን ምነው ባልተጣራ ዜና እስልምና ላይ ጣት ይቀስራሉ። ጨዋዉን የሙስሊሙ ማህበረሰብ አያውቁትም እንዴ። ከማንም በፊት ቀድሞ ሰላማዊ ትግል በአገራችን ኢትዮጵያ ያስተዋወቀው ሙስሊሙ ማህበረሰብ መሆኑ አያስታውሱም እንዴ? ይህን ከማንም በፊት ቀድሞ የነቃ ማህበረሰብ እንዴት ቢንቁት ነው ለማንም ኩታራ ጥሪ ምላሽ ይሰጣል ብለው የገመቱት? የኢትዮጵያ ሙስሊም ከእስልምና እምነቱ እኩል አገሩን ያከብራል። ምንም እንኳን ሁሌም እንደባይተዋር እየታየ የኖረ ማህበረሰብ ቢሆንም ለኢትዮጵያ ህይወቱን ሲሰጥ የኖረ ህዝብ ነው። ለዚህ ህዝብ ክብር እንጂ እንዲህ ያለ የወረደ ነገር አይገባውም። መልካም ምሽት
ዌልካም አቶ ጀማል! (ዞረው ካልገቡ በስተቀር ) እንደ እንግዳኖቶ በዌልካም ብቻ ልቀበሎ። እንጂ ተላልፈናል።
Jemal wrote: Wed Jan 10, 2024 9:35 pmሠላም የዚህ ፎረም ተሳታፊዎች
አቶ ዳን ምነው ባልተጣራ ዜና እስልምና ላይ ጣት ይቀስራሉ። ጨዋዉን የሙስሊሙ ማህበረሰብ አያውቁትም እንዴ። ከማንም በፊት ቀድሞ ሰላማዊ ትግል በአገራችን ኢትዮጵያ ያስተዋወቀው ሙስሊሙ ማህበረሰብ መሆኑ አያስታውሱም እንዴ? ይህን ከማንም በፊት ቀድሞ የነቃ ማህበረሰብ እንዴት ቢንቁት ነው ለማንም ኩታራ ጥሪ ምላሽ ይሰጣል ብለው የገመቱት? የኢትዮጵያ ሙስሊም ከእስልምና እምነቱ እኩል አገሩን ያከብራል። ምንም እንኳን ሁሌም እንደባይተዋር እየታየ የኖረ ማህበረሰብ ቢሆንም ለኢትዮጵያ ህይወቱን ሲሰጥ የኖረ ህዝብ ነው። ለዚህ ህዝብ ክብር እንጂ እንዲህ ያለ የወረደ ነገር አይገባውም። መልካም ምሽት
የዚህን ዜና እውነተኛነት ለማረጋገጥ ስንበረብር፣ የአልሸባብ ቃል አቀባይ ከ10 ቀናት በፊት ይህን ጥሪ ማድረጋቸውን የሚጠቁም መረጃ አገኘን። ለጊዜው በየትኛው ሚድያ ይህን ጥሪ እንዳስተላለፉ ለማወቅ አልቻልንም። ይዘቱን እዚህ ላይ ለጥፈነዋል።
የወደብ ስምምነቱ የፈጠረው ውጥረት አልሸባብን የሚያጠናክር መሆኑን የገመተው ጽሁፍ፣ ብዙም ሳይቆይ ከሳምንት ብኋላ አል ሸባብ የተመድ ሄልኮፕተር ጠልፏል። በውስጧ የነበሩ ሰዎች እስካሁን የት እንዳሉ አልታወቀም። ፖሊስ አሰሳውን እንደቀጠለ ነው።
ጽሁፉ አልሸባብ ኢትዮጵያን እንደ እስራኤል እንደሚመለከታት ይገልጻል። እስራኤል ቀስ በቀስ ፍልስጤምን እንደሰለቀጠቻት ሁሉ የኢትዮጵያም ፍላጎት ሶማሊያን መሰልቀጥ ነው ይላል። ስለሆነም ለጅሀድ ተነሱ የሚል ጥሪ ማስተላለፉ ታውቋል።
ይህ አይነት ጥሪ በአልሸባብ ሁሌም ሲባል የኖረ እንደመሆኑ መጠን ብዙም ትኩረት ላንሰጠው እንችላለን። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍልና ቀውስ እንዲህውም ሶማሊያ ላይ እየተፈጠረ ያለው ናሽናሊስቲክ እንቅስቃሴ ተዳብለው ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት መሰንዘር አይችሉም ብሎ መገመት ያስቸግራል።