ውሃ ውስጥ መጻፍ

water

ጽህፈት (መጻፍ) ቢያንስ ለ30,000 ዓመታት የቆየ የመገናኛ ዘዴ ነው። ዘመናዊ የአጻጻፍ ቴክኒኮች ብዙውን ጊዜ በጠጣር ንጣፎች (solid surfaces) ላይ መቅረጽ ወይም ቀለም መጠቀምን ያካትታሉ። ይሁን እንጂ በፈሳሽ ውስጥ መጻፍ ከዚህ በፊት ያልተለመደና ፈጽሞ የተለየ አቀራረብን የሚጠይቅ ነው።

በጀርመን የጆሃንስ ጉተንበርግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የኮሎይድል ቅንጣቶች በመባል የሚታወቁትን ጥቃቅን ቅንጣቶችን የስበት ኃይልን በመጠቀም ወደ መስመሮችና ቅርጾች በማደራጀት ፊደሎችን እና ውስብስብ ንድፎችን በውሃ ውስጥ መጻፍና መሳል የሚቻልበትን የፈጠራ መንገድ አሳይተዋል።

ተመራማሪዎቹ  ከዩኒቨርሲቲያቸው ስም የመጀመሪያዎቹን ሆሄያት እና አንድ ቀላል የቤት ስዕልን ጨምሮ የተለያዩ ቃላትንና ቅርጾችን መጻችና መሳል ችለዋል። ይሁን እንጂ የሆሄያቱና ስዕሎቹ ቅርጾች ከ10 ደቂቃ በኋላ መስፋት (መጥፋት) የጀመሩ ሲሆን፣ በአልትራቫዮሌት ብርሃን (UV light) አማካኝነት በቋሚነት በቦታቸው ማቆየት እንደሚቻል ተመራማሪዎቹ ጠቁመዋል።

ምንጭ፥ https://arxiv.org/abs/2304.05357

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply