ተጠየቅ

ከማእድን ሚንስቴር ድረገጽ የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ከወርቅ ቀጥሎ እምቅ የplatinum, copper, potash, natural gas እና hydropower ሀብት አላት፣ tantalum የሚባል ማዕድን ለዓለም ገበያ ኤክስፖርት ከሚያደርጉ ግንባር ቀደም አገራት መካከል አንዷ ናት፣ ከነዚህ ማዕድናት በተጨማሪ ሰፊ የniobium, platinum, tantalite, cement, salt and gypsum, clay and shale, and soda ash ክምችት እንዳላት ይገለጻል። ነገር ግን ከዚህ ዘርፍ የሚገኘው ገቢ ከአገሪቱ አመታዊ ገቢ አንድ መቶኛ (1% በታች) እንደሆነ ነው የሚነገረው። ትኩረት ተነፍጎት ነው? ሌብነት ነው? ወይስ በቂ የተማረ የሰው ሃይል ስሌለ ነው?

ተፈጥሮ ለኛ አድልታ የለገሰችንን ሀብት እንዴት በአግባቡ መጠቀም ይሳነናል? የወርቅ ክምችቱማ ፈረንጆቹን አፋቸውን በመዳፋቸው አስይዟቸዋል። አገሪቱ ያልተነካ የወርቅ ክምችት ላይ ነው የተቀመጠችው ሲሉ ይደመጣሉ።። እነ Apple በየቦታው ለጉድ የሚቀራመቱት cobaltም በአገራችን እንደሚገኝ ይገለጻል። ነዳጅ መገኘቱንም ሰምንተን ነበር።። ሠፊ፣ ለምና ውሃ ግቡ የሆነ የእርሻ መሬትም ታድለናል። ከምንም በላይ ደግሞ በአፍሪካ ከትላልቅ አገራት ተርታ የሚመድበት የሰው ሀብት፣ የህዝብ ብዛት አለን። በብዙዎች ለገበያ ይፈለጋል። ደጃችንን የሚጠኑ የውጭ ባለሀብቶች ብዙ ናቸው። (በዛው ልክ ሲያኮርፉ ባልበላው ለምን አልበትነው የሚሉም ብዙዎች ናቸው።)

ጂኦፖለቲካሊ ተፈጥሮ ቁልፍ ቦታ ላይ አስቀምጣናለች። ከአሜሪካና እስራኤል ጀምሮ እስከ ቻይናና ራሽያ እንዲህውም ዓረብ አገራት ድረስ የሚያፋጭ ቁልፍ ቦታ ላይ ተቀምጠናል። የአየር ጸባዩ፣ ብዝሀ ህይወቱ፣ ምኑ ተፈጥሮ ለኛ ማዳላቷን የሚመሰክሩ ልዩ ሀብታችን ናቸው። ልክ እንደዚህ ሁሉ የባህል ብዝሀነቱ ጥሬ ሀብት ነበረ። በቋንቋ፣ በብሔር፣ በእምነት፣ በቆዳ ቀለም፣ ዳይቨርሲፋይድ የሆኑ፣ ነገር ግን ለምዕተ ዓመታት አብረው መኖር የቻሉ፣ ከዛም አልፈው ከአንድም ሁለት ሶስቴ ከውጭ ወራሪ ራሳቸውንና አገራቸውን ተባብረው ማስጠበቅ የቻሉ፣ የዓለምን ታሪክ እስከወዲያኛው የቀየሩ፣ የራሳቸው ፊደላት ቀርጸው ታሪካቸውን በጽሁፍ ማኖር የቻሉ ዜጎች ኖረው ያለፉባት፣ በአንድ ወቅት ገናና ኢምፓየር የነበረች አገር ባለቤት ነበርን።

ይህን ሁሉ የተፈጥሮ ፀጋ፣ የቅርስና የታሪክ ሀብት ታቅፈን ከአፍንጫችን ጫፍ በላይ አሻግረን ማየት ስለተሳነን፣ የራሳችንን ህይወት ከመቀየር አልፎ እንደ አያቶቻችን ዓለምን መለወጥ የምንችልበት እድል እያለን፣ ራእይ አልባ ሆነን በመንደር ታጥረን፣ እርስ በእርስ እየተፋጀን እውቀትና ቴክኖሎጂ ባልነበረበት ግዜ ከኖሩት አያት ቅድመ አያቶቻችን የከፋ የድንቁርና የፅልመትና የውርደት ኑሮ እንኖራለን። መቼ ነው ክፋት የሚበቃን? መቼ ነው የምንነቃው??

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply