የፕሮፌሰርነት ማዕረግ አሰጣጥ ሂደትና ተግዳሮቱ

DW የጀርመን ድምፅ ራድዮ

ባለፈው ሳምንት የአዲስ አበባ እና የሀዋሳ ዩኒቨርስቲዎች ለ10 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥተዋል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያሉ ፕሮፌሰሮች ግን ጥቂት መሆናቸውን የሚጠቆሙት የዘርፉ ባለሙያዎች በአንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሊኖር ይገባል ከሚባለው ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ክፍተት እንደሚስተዋል ይጠቁማሉ፡፡

በአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ መካከል 50 ዓመት ገደማ ልዩነት አለ፡፡ ሰላሳ ሶስት ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር የጀመረው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አሁን 50 ሺህ ተማሪዎች ትምህርት የሚገበዩበት ተቋም ሆኗል፡፡ ከተቋቋሙ 40 ዓመት የሞላቸውን ኮሌጆች ጭምር በውስጡ ያቀፈው ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በበኩሉ 40 ሺህ ገደማ ተማሪዎች እያስተናገደ ነው፡፡ ሁለቱም ዩኒቨርስቲዎች ከዓመት ዓመት የሚሰጧቸውን የትምህርት ዘርፎች እያስፋፉ፣ የቅበላ አቅማቸውንም እያሳደጉ ቢመጡም የሚጋሩት መሰረታዊ ችግር አለ፡፡

ሁለቱም አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሊኖረው የሚገባውን ያህል የዶክትሬት ዲግሪ የያዙና እና የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ላይ የደረሱ በርካታ ምሁራን የላቸውም፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ካሉት መምህራን መካከል የሙሉ ፕሮፌሰሮች ቁጥር ከሶስት በመቶ እንደማይበልጥ ሰሞኑን የወጣ አንድ መረጃ ይጠቁማል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያላቸው ምሁራን ዘጠኝ ብቻ ነበር፡፡

ለመሆኑ በአንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ካሉ ምሁራን መሀል ምን ያህሉ ሁለተኛ ዲግሪ፣ ምን ያህሉ የዶክትሬት ዲግሪ ማዕረግ ሊኖራቸው ይገባል? ፕሮፌሰሮች? በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖሊሲ እና ልማት ተቋም ዳይሬክተር እና በስነ-ትምህርት ዘርፍ የተመረቁት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ሰመላ ምላሽ አላቸው፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለመከታተል እዚህ ይጫኑ

0 replies

Leave a Reply

Leave a Reply