Page 1 of 1

ከዩትዩብ በነጻ ኦዲዮና ቪድዮ ያለ አፕና ኤክስቴንሽን ለማወረድ

Posted: Sun Jan 28, 2024 11:03 pm
by Kitaw

አዳዲስ ሙዚቃዎችና የተለያዩ ይዘት ያላቸው በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ቪድዮዎች በየቀኑ በዩትዩብ ይሰቀላሉ። ይዘቶቹን ለማውረድ ፕሪሜር ተጠቃሚ መሆንን ይጠይቃል። አሊያም ለዚህ ተብለው የተሰሩ አፕሊኬሽኖችንና ኤክስቴንሽኖችን መጫን ያስፈልጋል። እነዚህ አፕሊኬሽኖችና ኤክስቴንሽኖች ፍራንክ ባይጠይቁም፣ በከፍተኛ መጠን የሚተመን መረጃ ከተጠቃሚው ይሰበስባሉ። ሰብስበው መረጃውን ለ3ኛ አካል ይሸጣሉ። እነዚህ 3ኛ ወገን አካላት ከነጉግል ፌስቡክ ትዊተርና የመሳሰሉ ኩባንያዎች በከፍተኛ ዋጋ ተመሳሳይ መረጃ ከመግዛት ከነዚህ ጥቃቅን የሚመስሉ አፕሊኬሽንና ኤክስቴንሽኖች ቀለል ባለ ዋጋ መግዛት ይመረጣሉ። ምናልባትም አንዳንዶቹ ህገወጥ የሆነና ጭራሽ ተጠቃሚው የማያውቀው ያልተለመደ መረጃ እየተሰበሰበበት ሊሆን ይችላል። ለዚህም ሲባል ብዙ ጊዜ የነጻ የሚመስሉ ፕሮግራሞችን ማውረድ አይመከርም። ታድያ የመክፈል አቅም የሌለው እንዴት እነዚህን ነገሮች ህጋዊ በሆነ መንገድ በነጻ ማግኘት ይችላል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ጥያቄው ተገቢ ነው። መልሱ ቀለል ያሉ ፕሮግራሞችን መማር ነው። ከዚህ ቀጥሎ የዩትዩብ ቪድዮና ኦድዮ በ10 መስመር የፓይተን ኮድ እንዴት ማውረድ እንደሚቻል እናያለን። ተከታተሉ ።

Hidden Content
This board requires you to be registered and logged-in to view hidden content.

Re: ከዩትዩብ በነጻ ኦዲዮና ቪድዮ ያለ አፕና ኤክስቴንሽን ለማወረድ

Posted: Tue Jan 30, 2024 8:52 pm
by Kitaw

ዩትዩብ ቪድዮ ለማውረድ

Hidden Content
This board requires you to be registered and logged-in to view hidden content.