Page 1 of 1

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ለሪሰርች እንዴት መጠቀም ይቻላል?

Posted: Mon Jan 22, 2024 11:50 am
by dan

ገበታውያን ሆይ ከናንተ መካከል AIን ለሪሰርች የተጠቀመ አለ? እንዴት ነው አጠቃቀሙ? ለምሳሌ ሀሳቤን መጀመሪያ በጉራማይሌ ቋንቋ ጻፍኩና በጉግል አስተረጎምኩት ከዛ ለAI ግራመሩን አስተካክልልኝ ብዬ ስሰጣው ቀሽሮ መለሰልኝ። አስተካክሎ የሰጠኝን እንዳለ ብጠቀም የኔ ጭንቅላት ውጤት ነው የሚባለው ወይስ የAI ነው የሚባለው? ገጠመኝ ካላችሁም ጨማምራችሁ አውጉኝ።


Re: የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ለሪሰርች እንዴት መጠቀም ይቻላል?

Posted: Tue Jan 23, 2024 12:23 am
by Kitaw

ይሔ ነገር የሁሉም ጥያቄ ሳይሆን አይቀርም። በሪሰርች ዓለሙ የካበተ ልምድ ያላቸው የገበታ አባላት አሉ፣ አስተያየታቸውን ቢሰጡበት እኔም በጣም ደስ ይለኛል።

እንደው ትእዝብቴን ለማካፈል ያክል ግን አንዳንድ ጆርናሎች ኤአይ መጠቀምና አለመጠቀማችሁን በግልጽ ዲክሌር አድርጉ ማለት ጀምረዋል። ሶሻል ሚድያ ላይ የምናያቸው አንዳንድ አሳሳች መረጃዎች ለምሳሌ ከኤአይ ያገኘውኸውን ትንሽ ሞርደህ ማቅረብ ትክክል እንዳልሆነ በብዙ አጋጣሚዎች ታይተዋል። ከሪጀክሽን በላይ የከፋው ደግሞ ከታተመ ብኋላ ምን ያህሉ የኤአይ ውጤት እንደሆነ ታውቆ ሪትራክ ሲደረግ ነው። ለሲቪም ጥሩ አይሆንም። ውልግድግድ ያለውን ረቂቅ ለአርታእያኑ መላክ ነው የሚሻለው። ምን ላይ ነው እየሰራህ ያለኸው?ኢፍ አይ መይ አስክ :)