ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የቀረበ ጥሪ

CURRENT AFFAIRS IN ETHIOPIA AND THE REGION


Post Reply

Topic author
yay
Posts: 1
Joined: Wed Jan 10, 2024 9:35 am

የዚህ ጽሁፍ አላማ በሀገራችን እየተባባሰ በመጣው ጦርነትና ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተከሰተው ርሀብና ድህነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተልእኮ ላይ የሀሳብ ልውውጥ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ከሀይኖት ይልቅ ለፖለቲካ በቀረበ ርእሰ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ትርጉም ያለው ተጽዕኖ የላትም በሚል እሳቤ በርካቶች ጉዳዩን አሳንሰው ሊያዩት ይችላሉ፡፡ ነገሩ ግን ወዲህ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊና በርከታ ምእመናንን የቀፈች በመሆኑ በኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ባህላዊ ህይወት ውስጥ ጉልህ ሚና አላት፡፡ የቤተክርስቲያኗ አሻራ በኢትዮጵያ ታሪክ፣ ሥነ-ጽሁፍ፣ ኪነጥበብ፣ የትምህርት ስርአት፣ ባህልና አስተሳሰብ ላይ በጉልህ ይታያል፡፡ ስለዚህ ጦርነትን በማስቆም፣ ርሀብና ድህነትን በመከላከልና ሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የቤተክርስቲያኗን ሚና አሳንሶ ማየት አይቻልም፡፡
እርግጥ ነው ሀገሪቱ በምትመራበት ህገ-መንግስት መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ መሆናቸው ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ወደ 98 በመቶ ህዝቧ አማኝ በሆነበት ሀገር የሀይማኖት ተቋማትን ሚና መዘንጋት ከዕውነታው መራቅ ነው፡፡ ስለዚህም የሀይማኖት ተቋማት ጦርነትን በማስቆም፣ ግጭቶችን በመከላከል፣ የግጭት ተፈናቃዮችን በመርዳትና መልሶ በማቋቋም፣ ለረሀብ ለተዳረጉ ወገኖች የእለት ደራሽ እርዳታ በማቅረብና ሌሎች ድጋፎችን በመስጠት የላቀ ሚና አላቸው፡፡
ትኩረታችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስለሆነች በዚህ ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ በወደቀችበት ወቅት ቤተክርስቲያኗ ምን ማድረግ ትችላለች የሚለውን ጉዳይ በጥቂቱ እንቃኝ፡፡ በመጽሀፍ ቅዱስ በሉቃስ ወንጌል በምእራፍ 14 ከቁ 12 – 14 ቸርነትንና በጎ ተግባርን በተመለከተ የሚከተለው ሰፍሮ ይገኛል ፡-
እየሱስም የጋበዘውን ሰው እንዲህ አለው:- “የምሳ ወይም የራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ጓደኞችህን ወይም ወንድሞችህንና እህቶችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ሀብታም ጎረቤቶችህን አትጥራ። ምክንያቱም እነሱም አንድ ቀን ሊጋብዙህና ብድር ሊመልሱልህ ይችላሉ። ሆኖም ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ አካለ ስንኩላንን፣ አንካሶችንና ዓይነ ስውሮችን ጥራ፤ ትባረካለህና። ብድራትህን ባይመልሱም በጻድቃን ትንሣኤ ብድራትህ ይመለስልሃል።”
ሀገራችን ኢትዮጵያ በዚህ በጦርነት በደቀቀችበትና ረሀብ በጠናበት ቀውጢ ወቅት ይህ ከላይ የተጠቀሰውን አስተምህሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከምንግዜውም በላይ ተግባራዊ ልታደርገው የሚገባት ተልዕኮ ነው፡፡ በመቀጠልም የሀይማኖቱ ተከታይ ምእመናን ይህን ትምህርት በልባቸው አሳድረው እጃቸውን መዘርጋት ያለባቸው ወቅት አሁን ነው፡፡ የሌሎች ሀይማኖት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያውያንም በሰብአዊነት መንፈስ ለወገን ደራሽ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሀገሪቱ በታላቅ የቀውስ ማዕበል እየተናወጠች ነው፡፡ እንደ ሀገር ክፉኛ ተከፋፍለናል፡፡ የአንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጽኑ አማኞች ቢያንስ ቢያንስ ለሁለት ተከፍለናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነውና አደገኛው ጉዳይ ደግሞ እነዚህ ለሁለት የተከፈሉት የአንዲቷ ቤተክረስቲያን ጽኑ አማኞች አሁን የተከሰተውን አለመግባባትና ግጭት መፍታት የሚቻለው በጦርነት ብቻ ነው ብለው ማመናቸው ነው፡፡
ግን ሀቁ እንዲህ ነው? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልብ ብለን እናጢን፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ህልውና ላይ የራሷ የሆነ ጉልህ ሚና እንዳላት ሁሉ በማያወላደ ሁኔታ ለያንዳንዱ ግለሰብና አካባቢ ሰላም አትተጋም?
ቤተክርስቲያኗ ጦርነት እንዳይቀሰቀስና ከተቀሰቀሰም እንዲቆም ድምጽዋን አታሰማም?
በግጭት የተጎዱ ማህበረሰቦችና ግለሰቦችን ለመርዳት ወሳኝ የሆነውን ሀላፊነቷን አትወጣም?
ምንም አይነት አድልዎ ሳታደርግ ከሌሎች የሀይማኖት ተቋማት ጋር በመተባባር እንደ መጠለያ፣ ምግብና አልባሳት ያሉትን ድጋፎች ለተጎጂዎች አታቀርብም?
ለነዚህ ጥያቄዎች የተለያዩ መልሶች እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ ጥያቄዎቹ ክርክርም ሊያስነሱ ይችላሉ፡፡ ዋናው ነገር ግን ክርክሩን ወደ ውይይት ቀይሮ መፍትሄ መስጠት ነው፡፡ እንደ ተቋም የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች እንደ ማህበረሰብም ልንጠየቅባቸው እንችላለን፡፡
እንደ ማህበረሰብ እንደ ህዘብ እኛስ የእርስ በርስ ጦርነቱና የረሀቡ ሰለባ የሆኑ ወገኖቻችንን የሚገባንን ያህል ደግፈናል ?
ፈተና ውስጥ የወደቁ ዜጎችን ለመርዳት ምን የተጨበጠ እርምጃ ወስደናል?
የተፈናቀሉትንና በድህነት አረንቋ ውስጥ የወደቁትን ወገኖች አንገብጋቢ ችግሮች ለመቅረፍ አቅማችንን አስተባብርን እርምጃ ወስደናል?
የችግሩ ሰለባ የሆኑ ወገኖችን ለመደገፍ ከላይ በተተቀሰው አስተምህሮ መሰረት ብድራት ሳንጠብቅ የቸርነትና የበጎ ተግባር ባህል አዳብረናል?
በማሳረጊያውም የጽሁፋችን ርዕሰ ጉዳይ ወደ ሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን እንመለስ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ሀገራችን ወደማያባራና የለየለት የእረስ በረስ ጦርነት እንዳትገባ እየተጋጋለ የመጣውን ‹‹ የውረድ እንውረድ›› እልክና ደምፍላት ለማብረድ ተቋማዊና ታሪካዊ ሚናዋን መጫወት ይጠበቅባታል፡፡ ቤተ-ክረስቲያኗ በመርህ ደረጃ ሁሉንም አይነት የሀይል እርምጃዎች ማውገዝ የሚኖርባት ሲሆን ወደ ግጭትና ጦርነት ከሚመሩ ሀሳቦችና መግለጫዎች ራሷን ማግለል የተልእኮዋ አካል ማድረግ ይኖርባታል፡፡ በጦርነት የተፈናቀሉትን፣ በግጭና በድርቅ ለረሀብ የተጋለጡትንና የተራቡትን መደገፍ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው አስተምህሮ መሰረት የቤተክርስቲያኗ ሀዋርያዊ ተልእኮ ነውና ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ይህን ግዙፍ ሀገራዊ ተልእኮዋን ለመወጣት ከሁሉም ነገር በፊት ጓዳዋን ማጽዳት አለባት፡፡ አደረጃጃቷን በሀቀኝነት ፈትሻ ከወቅቱ ጋር ለመሄድ ማዘመን ይጠበቅባታል፡፡ ይህን ስታደርግ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ምዕመኗን ማሰባሰብና ግዙፍ አቅም መፍጠር ትችላለች፡፡ ይህን ማድረግ ከቻለች ቤተክርስቲያኗ ሀገራችንን ከውድቀት ከመታደግ አልፋ የቸርነትና ተባብሮ የመስራት ፣ የውጤታማ ወይይት፣ የመከባባርና የፍቅር ማዕከል ትሆናለች፡፡ እንዲ አንዲሆን ተስፋ እናድርግ?


ZaraYaqob
Posts: 7
Joined: Sun Sep 03, 2017 12:55 pm

የኦርቶዶክስ ዲያቆኖች መንግስት በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ አይግባ የሚሉትን ያህል ዲያቆኖቹ በመንግስትና ፖለትካ ጉዳይ ጣልቃ ባይገቡ ዛሬ አገሪቱ እዚህ ትርምስ ውስጥ አትገባም ነበር። በድቁና እውቀታቸው የመንግስት አማካሪ ሆነው በትግራይና በኦሮሞ ህዝብ ያደረሱት እልቂት አሁንም በአማራ ህዝብ እያደረሱት ያለው ውድመት በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ አይታወቅም። የሃይማኖት ሰዎች ፖለቲካ ውስጥ ፈጽሞ መግባት የለባቸውም። የሃይማኖት ተቋማቱ እንደማንኛውም ተቋም በአገሪቱ ህግ መመራትና ህጉን ማክበር እስካለባቸው ድረስ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሊሆኑ አይችሉም። መንግስት ህግ ማስከበር ስላለበት። የሰሩትን እየሰሩ በሃይማኖት ሽፋን መደበቅ የለም።


dan
Posts: 20
Joined: Mon Apr 13, 2020 11:52 pm

:lol: :lol:

ZaraYaqob wrote: Wed Jan 10, 2024 6:03 pm

የኦርቶዶክስ ዲያቆኖች መንግስት በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ አይግባ የሚሉትን ያህል ዲያቆኖቹ በመንግስትና ፖለትካ ጉዳይ ጣልቃ ባይገቡ ዛሬ አገሪቱ እዚህ ትርምስ ውስጥ አትገባም ነበር። በድቁና እውቀታቸው የመንግስት አማካሪ ሆነው በትግራይና በኦሮሞ ህዝብ ያደረሱት እልቂት አሁንም በአማራ ህዝብ እያደረሱት ያለው ውድመት በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ አይታወቅም። የሃይማኖት ሰዎች ፖለቲካ ውስጥ ፈጽሞ መግባት የለባቸውም። የሃይማኖት ተቋማቱ እንደማንኛውም ተቋም በአገሪቱ ህግ መመራትና ህጉን ማክበር እስካለባቸው ድረስ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሊሆኑ አይችሉም። መንግስት ህግ ማስከበር ስላለበት። የሰሩትን እየሰሩ በሃይማኖት ሽፋን መደበቅ የለም።


Jemal
Posts: 2
Joined: Wed Jan 10, 2024 9:05 pm

ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በሃይማኖት መቻቻል ይገለጣል። የሌሎችን እምነት ስናከብር የራሳችንን አከበርን ማለት ነው። ከውጭ ሆኘ ስመለከት ይህ ፎረም ሳይንሳዊ ውይይት የሚደረግበት መስሎኝ ነበር። መጀመሪያ አካባቢ ደግሞ እንደዛ ነበር። የሰው እምነት ማራከሱን ትታችሁ የሳይንስ እውቀት ካላችሁ እስኪ አካፍሉን።

Post Reply