አራቱ የኢትዮጵያ ህገ-መንግስታት

FACTS ABOUT ETHIOPIA AND THE REGION


User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

በአብዛኛዉ የታሪክ ክፍል የኢትዮጵያ አስተዳደር በሁለት ቁልፍ ሰነዶች ይመራ ነበር፡ ክብረ ነገስት እና ፍትሀ ነገስት። በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጻፈው ክብረ ነገስት፣ የስልጣን ምንጭ ከሰለሞናዊው ስርወመንግስት የሚመነጭ መሆኑን ያስቀምጣል። በ13ኛው ክፍለ ዘመን በአረብኛ የተጻፈው እና ኋላም ወደ ግእዝ የተተረጎመው ፍትሀ ነገስት በበኩሉ፣ የቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንቦችንና የፍትሐ ብሔር ሕጎችን ይዘረዝራል። እነዚህ ሁለቱ ሰነዶች በአተገባበሩ ላይ ልዩነቶች ቢኖራቸውም፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ተፅዕኖ በመፍጠር ረገድ አቻ የሌላቸው ቁልፍ ሰነዶች ነው።

ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ በአራት ሕገ መንግሥታት ተስተዳድራለች። በ1930ዎቹ በአጼ ሀይለስላሴ ለመጀመሪያ ግዜ በስራ ላይ የዋለ ህገመንግስት፣ ልክ እንደ ክብረነገስት ሁሉ፣ የስልጣን ምንጭ ከሰለሞናዊው ስርወ መንግስት እንደሚመነጭ ይጠቅሳል። ይህ ህገመንግስት ተስፋ ሰጪ የሪፎርም አንቀጾችን አካትቶ የነበረ ቢሆንም፣ አብዛኛውን ስልጣን ለንጉሰ ነገስቱ በመስጠት፣ በዋናነት ህጋዊነትን የማላበስ ድርሻ ይጫወታል።

በ1950ዎቹ ተሻሽሎ የቀረበው የዚሁ ህገመንግስት ቅጥያም፣ አንዳንድ ተጨማሪ መብቶችን አካትቶ የነበረ ቢሆንም፣ ቀዳሚ ሚናው አሁንም ለንጉሰነገስቱ ስልጣን ህጋዊ ሽፋን መስጠት ነው። በ1970ዎቹ ይህንኑ ህገመንግስት ለሶስተኛ ግዜ ለማሻሻል፣ ረቂቅ ተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን፣ በአብዮቱ ምክንያት ወደ ተግባር ሳይቀየር ተጨናግፎ ቀርቷል።

ዘውዳዊው ስርዓትን በመፈንቅለ መንግስት ገርስሶ ስልጣን ላይ የተቀመጠው የደርግ ስርዓት በበኩሉ የራሱን ህገመንግስት ስልጣን ከያዘ ከ10 ዓመት ብኋላ ያጸደቀ ሲሆን፣ ከራሺያዊ ኮሚኒስት ፓርቲ እንደወረደ የተቀዳ እንደነበር የሚናገሩት ብዙዎች ናቸው። ይህ ህገመንግስት የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲን (ኢሰፓ) ወሳኝ ስልጣን በማላበስ፣ በአገሪቱ ጉዳይ ፈላጭ ቆራጭ ሀይል አድርጎ ያስቀምጣል። በሰብአዊ መብቶች ረገድ፣ አሁን በስራ ላይ ካለው ህገመንግስት ያልተናነሰ ድንጋጌዎች የነበሩት ቢሆንም፣ በተግባር ወታደራዊው ስርዓት ለነዛ መብቶች ቁብ የማይሰጥ እንደነበረ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ጉዳይ ነው።

አራተኛውና ከ1987 ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በስራ ላይ ያለው ህገመንግስት፣ በዋናነት የሚታወቀው፣ ለብሔር ብሔረሰቦች ልዩ መብት (እስከመገንጠል ድረስ) የሚያጎናጽፍ መሆኑ ነው። በኢህአዴግ መሪነትና አብላጫ ድምጸ ውሳኔ የጸደቀው ይህ ህገመንግስት፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ለምትገኝበት የእርስ በእርስ ግጭትና ቁርቁዝ፣ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚናገሩት ብዙዎች ናቸው። እንደነዚህ ተከራካሪዎች አባባል፣ ብሔሮችን እክስመገንጠል ድረስ የሚያጎናጽፍ ያልተገደበ መብት፣ በፖለቲከኞች መካከል አለመግባባት ሲፈጠር፣ መገንጠልን እንደፖለቲካ ካርድ የመጠቀም አዝማሚያ እንዲኖር አስተዋጽኦ አድርጓል ይላሉ። በሌላ በኩል ለብሔሮች እውቅና የማይሰጡት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ህገመንግስታት፣ በአንድ ብሔር የበላይነት ተቀርጸው፣ አሃዳዊ ስርዓት በህዝቦች ላይ በግድ እንዲጫን አድርገው የነበረ በመሆኑ፣ የመገንጠል ጥያቄ አነግበው የተነሱ በርካታ ቡድኖች እንደነበሩ የሚያወሱ ተከራካሪዎችም አሉ። በመሆኑም ይላሉ እነዚህ ተከራካሪዎች፣ የመገንጠልና የእርስ በእርስ ግጭት አደጋው ያኔም በተጨባጭ ታይቶ ነበረ። እነዚህ ክርክሮች በጋራ የሚጠቁሙት ነገር ቢኖር የተሻለው አማራጭ ያለው በሁለቱ መካከል መሆኑን ነው። ምናልባትም ለዘላቂ ሰላምና አብሮነት ሲባል ሁሉንም ግምት ውስጥ ያካተተ ህገመንግስታዊ ማሻሻያ ማድርገ ተገቢ ይሆናል።

አራቱን የኢትዮጵያ ህገመንግስታት፣ ከአጭር መግቢያና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች ጋር፣ በኢንግሊዝኛ ቋንቋ በመጽሃፍ መልክ በልዩ ሁኔታ ተሰንዶ እዚህ ላይ ቀርቧል። ለወዳጅ ለዘመድ፣ ለጓደኛ ያካፍሉ።

የገና ስጦታዬ ነው ወዳጆች! ጤና ይስጥልኝ!

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Kitaw
Posts: 22
Joined: Sun Sep 03, 2017 6:09 pm

@yaman it is official, you are my favorite blogger. You are so inspiring. Pls keep up the good work.


ZaraYaqob
Posts: 7
Joined: Sun Sep 03, 2017 12:55 pm

I agree with you, @Kitaw . This is so inspiring. Thank you @yaman as usual for sharing such great stuffs! Merry X-mass to all :!:

Kitaw wrote: Tue Dec 26, 2023 8:15 pm

@yaman it is official, you are my favorite blogger. You are so inspiring. Pls keep up the good work.

User avatar

Baykedagn
Posts: 13
Joined: Sun Sep 03, 2017 6:39 pm

ድንቅ ስራ ነው የሙ ቀጥልበት። ሊንኩን ቡክማርኬ ላይ አካትቸዋለሁ።

yaman wrote: Tue Dec 26, 2023 6:53 pm


አራቱን የኢትዮጵያ ህገመንግስታት፣ ከአጭር መግቢያና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች ጋር፣ በኢንግሊዝኛ ቋንቋ በመጽሃፍ መልክ በልዩ ሁኔታ ተሰንዶ እዚህ ላይ ቀርቧል።

"Reason has always existed but not always in a reasonable form." KM
User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

አመሰግናለሁ ወዳጆቼ :!: :!: መልካም የገና በዓል ለሁላችሁም 🎄🎄

@Kitaw እድሜ ላንተ ነው ወንድም አለም፤ ያኔ ላቴክስ እዚህ ጀማምረህልን፣ ወስውሰሀን፣ አስተምረሀን ነው፣ ለዚህ የበቃነው። የምናቅህ እንመስክርልህ እንጂ አንተማ ደፍረህ አትወጣትም :)

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Kitaw
Posts: 22
Joined: Sun Sep 03, 2017 6:09 pm

I know you are so humble, @yaman . Everyone in this thread would agree with me on that. Thanks though ;)

By the way, do you by an chance have the Amharic versions of previous constitutions?

yaman wrote: Tue Dec 26, 2023 9:13 pm

አመሰግናለሁ ወዳጆቼ :!: :!: መልካም የገና በዓል ለሁላችሁም 🎄🎄

@Kitaw እድሜ ላንተ ነው ወንድም አለም፤ ያኔ ላቴክስ እዚህ ጀማምረህልን፣ ወስውሰሀን፣ አስተምረሀን ነው፣ ለዚህ የበቃነው። የምናቅህ እንመስክርልህ እንጂ አንተማ ደፍረህ አትወጣትም :)

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

Thank you for the kind words wodaje @Kitaw. Unfortunately, I don't have the Amharic versions. But I would love to include them in the future.

Kitaw wrote: Wed Dec 27, 2023 12:20 am

By the way, do you by an chance have the Amharic versions of previous constitutions?

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

Post Reply