Page 1 of 1

ህዳሴ ግድብ መቼ ተጀመረ?

Posted: Tue Jan 26, 2021 1:51 am
by gebetaforum

በወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የመሰረት ድንጋይ በመጣል በዕለተ ቅዳሜ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ተጀመረ።

ስሙም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተብሎ ተሰየመ። በኢንግሊዝኛ ደግሞ The Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) ተባለ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ መሰረተ ድንጋዩን ሲጥሉ እንዲህ አሉ፥ « ... የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የላብ ፊርማ ያረፈበት ግድብ በመሆኑ የህዳሴ ጉዟችን መሐንዲሶች እኛው፣ ግንበኞቹና ሠራተኞቹ እኛው፣ የፋይናንስ ምንጮችና አስተባባሪዎች እኛው፣ በአጠቃላይ የህዳሴ ጉዟችን ባለቤቶች እኛው መሆናችንን የሚያሳይ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታችን ነው።»

ዜናው በያኔው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በአሁኑ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለመላው ኢትዮጵያውያ ህዝብ በተመሳሳይ ቀን ታወጀ። ዕለተ ቅዳሜ፣ መጋቢት 24፣ 2003 ዓመተ ምህረት።

ሲጀመር ግድቡ 5250 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ የታሰበ ቢሆንም፣ በሂደት አቅሙን አሳድጎ ወደ 6000 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ ይገመታል።