Posted: Mon Apr 06, 2020 1:03 pm
ይቺን ተዓምረኛ ግራፍ ተመልከቷት። መድሀኒት የለሹ ኮረና፣ የዓለም ሃያላን አገራትን፣ ፊልም ላይ አክተራቸው የማይሞተው፣ ሁሉንም የሚያሸነፉትን ጭምር፣ ዕጣ ፈንታቸው በዚች ግራፍ ብቻ እንድትወሰን አድርጓል። ሌላ አማራጭ የለም። ግራፉ የሚያመላክተው የሚታመመው ሰው ብዛት ከግዜ አንጻር ነው። እየጨመረ፣ እየጨመረ ሄዶ የሆነ ሰዓት ላይ ፒኩ ላይ ይደርሳል። ይቆለላል። ምንም እርምጃ ካልተወሰደ ብዙ ሰው በአጭር ግዜ ይታመማል፣ ቶሎ ፒኩ ላይ ይደርሳል፣ ፒኩ ደግሞ የትየሌለ ነው። ይህ በመንግስት፣ ሎጂስቲክ አቅርቦትና በህክምና ባለሞያዎች የሚፈጥረው ጫና (burden ) ከፍተኛ በመሆኑ የሚሞተው ሰውም በዛው ልክ ይሆናል። የሚሞተው ብዛት በሚልዮኖች ይገመታል። በአሜሪካ ከ2ሚልዮን በላይ ተግምቷል።
በሌላ በኩል ደግሞ ቀድሞ እርምጃ ከተወሰደ፣ የበሽታውን ስርጭት በማዘግየትና በመቀነስ፣ አንድም ቶሎ ፒኩ ጋ እንዳይደርስ፣ ሁለቱም ስርጭቱን በማራዘም ፒኩን ማሳጠር ይቻላል። ማለትም በአንድ ግዜ ብዙ ሰው ከሚታመም ይልቅ፣ በየጊዜው ትንሽ ትንሽ ሰው እንዲታመም ማድረግ ይቻላል ማለት ነው። ፒኩ (ጫፉ) ሲቀንስ በርደኑ (ጫናው) ይቀንሳል። ጫናው ሲቀንስ፣ የሎጂስቲክ አቅርቦት የተሻለ ይሆናል፣ ባለሞያዎችም ጫናቸው ስለሚቀንስ ብዙ ሰው ማትረፍ ይችላል። ስለሆነም የሚሞተው ሰው ቁጥር ይቀንሳል። አሜሪካ አሁን እየወሰደች ባለችው እርምጃ፣ የሚሞተው ሰው ብዛት እስከ ሁለት መቶሺ ድረስ ተገምቷል።
የሟቹን ቁጥር ከዚህም በታች ማውረድ ይቻላል። ነገር ግን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ይጠይቃል። አሁን በተወሰደው ቤዚክ እርምጃ አሜሪካ የ3 አመት የሚገመት ኢኮኖሚዋን ታጣለች። ማለትም ከበሽታው በፊት ወደነበረው የኢኮኖሚ ማማ ለመመለስ በትንሹ ሶስት አመት ይጠይቃታል።
ኮረና የሰው ህይወት ዋጋው ስንት ነው የሚለውን ከባድ የሞራል ጥያቄ እንድንጋፈጥ አስገድዶናል። የምንወስደው እርምጃ ኢኮኖሚክ ኮስቱንና ህዩማን ኮስቱን ያጣጣመ መሆን አለበት። ለምሳሌ አሜሪካ የሟቹን ቁጥር ከዛ በታች ለማውረድ ኢኮኖሚውን የባሰ ከጎዱት፣ እሱም ራሱን የቻለ ችግር ይፈጥራል። በስራ ማጣት፣ በድህነትና በሌላ ምክንያት ሊሞት ከሚችለው በተጨማሪ፣ ራሱን የሚያጠፋው ሰው ብዛት ቁጥርም ሊጨምር ይችላል። ለዚህ ነው፣ ራይት ባላንሱን መጠበቅ የሚያስፈልገው።