ከብዙ ክርክር ብኋላ አውሮፓ ለዘረመል ልውጥ ዘሮች እጇን በተወሰነ ደረጃ እየሰጠች ነው። ከሁለት አመት በፊት፣ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው 3 የበቀሎ ዝሪያዎች ለእንስሳት መኖነት ብቻ እንዲውሉ ፈቅዳ ነበር። ዘንድሮ ደግሞ ለምግብነት መዋል የሚችሉ መሆናቸውን ተቀብላለች። ነገር ግን አሁንም እነዚህን የበቆሎ ዝርያዎች ጨምሮ ማንኛውም የዘረመል ለውጥ የተደረገበት እህል በአውሮፓ ምድር ላይ ማብቀል የታገደ መሆኑን አሁንም በጽኑ አሳውቃለች። ሌሎች አገራት አምርተው፣ የዘረመል ለውጥ የተደረገበት መሆኑን በግልጽ ሌበል አድርገው፣ ወደ አውሮፓ ኤክስፖርት ማድረግ ይችላሉ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከጤነኛውና ኦርጋኒኩ ምርት በተለየ መልኩ እጅግ የረከሰ ስለሚሆን፣ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች (በአብዛኛው ኢምግራንቶች) የሚመገቡት ነው ሊሆን የሚችለው። ዞሮ ዞሮ ስደተኛው፣ በአገሩም ከአውሮፓም ውስጥ እንደ ጊኒፒግ የሙከራ ጣቢያ ሆኖ ያገለግላል።