ግጭት የማይለየው የአፍሪካ ቀንድ ተቧድኖ ፍጥጫ ውስጥ ገብቷል

CURRENT AFFAIRS IN ETHIOPIA AND THE REGION


Post Reply
User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ የወደብ ስምምነት ተከትሎ እየተፈጠረ ያለው ውጥረት ብዙዎችን የሚያሳስብ ሆኗል።

የሶማሊያው ፕሬዝደንት "ሶማሊያን ለመከላከል ከማንም ጋር እንተባበራለን" ባሉት መሰረት ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ኤርትራ ገብተዋል። ከፕሪቶሪያ ስምምነት ወዲህ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግኑኝነት ወደ ቀድሞው ሁኔታ ተመልሷል። የኢትዮጵያ መንግስት ስለ ቀይ ባህር በአደባባይ ማውራት ከጀመረ ወዲህ ሁለቱ አገራት ጦራቸውን ወደ ድንበር ማጋዝ እንደጀመሩ አለም አቀፍ ሚድያዎች መዘገባቸው ይታወሳል።

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ወደ ኤርትራ ባቀኑበት ዕለት፣ የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ጄነራሎች በአዲስ አበባ ተገናኝተው ወታደራዊ ውይይት አድርገዋል።

የሶማሌላንድ መከላከያ ሚኒስትር የወደብ ስምምነቱን በመቃወም ስልጣናቸውን ለቀዋል። ኢትዮጵያ የምን ግዜም ጠላታችን ሆና ሳለ 20 ኪሎሜትር ያክል ቤዝ መሰጠቷ ትክክል አይደለም፣ እኔ አልተስማማሁበትም የሚል ምክንያት ነበር ለመልቀቃቸው።

በሌላ በኩል ደግሞ አለም አቀፍ እውቅና የማግኘት እድሉ ሰፍቶ የታያቸው የሶማሌላንድ ዜጎች አደባባይ ወጥተው ሲጨፍሩና ደስታቸውን በሰልፍ ሲገልጹ ታይተዋል።

ዝርዝር ይዘቱን በገበታ ብሎግ ይከታተሉ።


dan
Posts: 20
Joined: Mon Apr 13, 2020 11:52 pm

አልሸባብ የተመድ ሄሊኮተር ዘረፈ ነው አወደመ እየተባለ ያለው? ደግሞ መረጃህ ምንድነው እንዳትለኝ አደራ። የወደብ ስምምነቱ ከማንም በላይ አልሸባብን ጠቅሞታል። እያየነው ነው።

User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

የአውሮፓ ህብረት፣ ቻይና፣ ቱርክና ግብጽን ጨምሮ በርካታ አገራት የሶማሊያ ሉኣላዊነት መከበር አለበት ሲሉ ድጋፋቸውን ለሶማሊያ ገልጸዋል። ቻይና እና ቱርክን ጨምሮ በርካታ ሃያላን አገራት ባህር ተሻግረው በአፍሪካ ቀንድ የራሳቸው ፖርት እንዳላቸው ይታወቃል። በቀይ ባህር ቀጠና ዛሬ እየታየ ያለው ቀውስ (የየመን ታጣቂዎች እየወሰዱት ያለውን እርምጃ ጨምሮ) እነዚህ ሃያላን አገራት ለየግል ጥቅማቸው በሚያራምዱት ጂኦፖለቲክስ ምክንያት የተፈጠረ መሆኑም ይታወቃል። ጦርነት ቢነሳም ለሁለቱ ወገን የጦር መሳሪያ በማቀበል ትርፍ የሚያጋብሱት እነሱው ናቸው።

Red-Sea-Reactions-Table.jpg
Red-Sea-Reactions-Table.jpg (250.07 KiB) Viewed 3903 times

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢጋድ ሶማሊያንና ኢትዮጵያን ሊያወያይ ለሚቀጥለው ሳምንት ቀጠሮ ይዟል።

እነዚህንና የመሳሰሉ ዜናና ትንታኔዎችን በብሎጋችን ያገኛሉ።

አንብባችሁ ከወደዳችሁት ወይም ከተማራችሁበት ሼር በማድረግ ገበታን ይደግፉ።

መልካም ቀን!

User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

ሶማሊያ በዲፕሎማሲው ረገድ እየመራች ይመስላል። በርካታ አገራትንና አለም አቀፍ ተቋማትን ከጎኗ ማሰለፍ ችላለች። የአረብ ሊግና ግብጽ ጠንከር ያለ መግለጫ ሁሉ አውጥተዋል። ግብጽ ሰበብ ነበር የምትፈልገው፣ ይህን አጋጣሚ ተጠቅማ ከአባይ ግድብ ድርድር ራሷን አግልላለች። ኤርትራንና ሶማሊያን ጋብዛ አነጋግራለች። በሶማሊያ ሉኣላዊነት የመጣ በአይኔ መጣ ብላለች። ይህ ሁሉ እምቡር እምቡር፣ ጫና በመፍጠር በግድቡ ላይ ፍላጎቷ ተፈጻሚ እንዲሆን ሌቨሬጅ መፍጠሯ ነው። በእርግጥ ግጭት ቢነሳ ትጥቅና ስንቅ ከማቀበል ወደ ኋላ አትልም። በቀጥታ ትሳተፋለች ወይም ግጭቱን ለመጫር ሰበብ ትሆናለች ብሎ መገመት ግን ይከብዳል። ያ ጣጣው ዘርፈ ብዙ እና ዘላለማዊ ነው። ለግጭት ቅስቀሳው ሻዕቢያ አለ። ሻዕቢያ የጀመራቸውን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ፣ ሶማሊያ እንደምንም ጦርነቱን እንድትጀምርለት ይፈልጋል። እያሰለጠነና አያስታጠቀም ነው። ለራሱም ከተደራጀ ቆይቷል። ከውስጥ ለጊዜው በአማራ ፋኖ ይተማመናል። ያው እንደተለመደው ቢሆንና በጥምረታቸው ትብብር የአብይ መንግስት እድሜው ቢያጥር፣ ፋኖና ሻዕቢያ መከሻከሻቸው አይቀርም። ታሪካቸውን ያውቃሉ፣ እንደተለመደው የጋራ ጠላት ለመምታት ለጊዜው ወደ ጎን ብለውታል።

ይህ እንዳይፈነዳ ስጋት ያደረባት አሜሪካ ሁለት ነገሮች ሞክራለች። አንደኛው በሻዕቢያ ላይ ለስለስ እንበል፣ እንደዶሮ ትንሽ ጥሬ በተን ብናደርግለት ይሻላል፣ ትኩረታችንን ነው የፈለው የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሲአይኤ ቺፍ ወደ ኬንያ በአካል ማቅናቱ ነው። ዝርዝሩን ብሎጋችን ላይ ታገኙታላችሁ።

በዚህ ውስብስብ ጉዳይ እነ አውሮፓ ህብረትን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት ባልተቀበሉት የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት፣ ኢትዮጵያ የመጣው ይምጣ ብላ ወደፊት ብትል፣ ማነው ሪስክ ወስዶ ወደቡን የሚሰራው የሚለው ጥያቄ መልስ ያገኘ ይመስላል። በኢሜሬት የሚገኝ አንድ ድርጅት ወደቡን ለመገንባት ተስማምቷል፣ እንደ ካፒታል ዘገባ ከሆነ። በእርግጥ ከዚህ ሁሉ ጀርባ ኢሜሬትስ እንዳለች የአደባባይ ሚስጥር ነው። አብይ አሕመድ ገና ወደ ስልጣን በመጣ ማግስት፣ ባህር ሃይሉን መልሶ እንዲያቋቁምና እንዲገነባ የገንዘብ ልገሳ ያደረጉለት (እና ለዚህ ያዘጋጁት) የምዕራቡ አለም አገራትም ከዚሁ ጀርባ እንዳሉ እሙን ነው። የአረብ ሊግ ተቃውሞም እንደሶማሌዎቹ ኢትዮጵያ ሶማሊያን አኔክስ ታደርጋለች በሚል ስጋት ሳይሆን፣ የጦር ቤዝ ትገነባለች ገንብታም የተቀናቃኞቻችንን ፍላጎት ለማስፈጸም ከኛ ጋር ትላተማለች በሚል ስጋት እንደሆነ ለመገመት አያዳግትም። የሆነው ሆኖ ፍጥጫው ቀጥሏል። የሰፊው የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ቅጥያ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች እየገለጹና እያስጠነቀቁ ነው።

ገበታ ዳይጀስት እንበላት እንዴ ይቺን?

User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

ሰላም እንዴት ሰነበታችሁ!

ኢንግሊዞች ለሶማሊላንድ እውቅና ለመስጠት ዳር ዳር እያሉ ነው። ዴቪድ ካሜሮን የየመኖቹን ሀውዚዎች ለመምታት ሶማሊላንድን እውቅና መስጠት ያስፈልጋል የሚል ሀሳብ ማቅረባቸው ተሰምቷል። ጉዳዩን የተለያዩ የኢንግሊዝ ሚድያዎች ዘግበውታል።

ለዚህ ሀሳባቸው የተሸፋፈነ ምክንያት ቢያቀርቡም፣ ዋናው ምክንያት የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት ተፈጻሚ ሆኖ ኢትዮጵያ ለምዕራባውያን የምትሰጠውን አገልግሎት በፍጥነት ማስጀመር ነው። ኢንግሊዞች እውቅና ከሰጡ ሌሎች ወዳጆቻቸውም ይከተላሉ። ኢትዮጵያ የባህር በር አግኝታ በበርበራ አካባቢ ከምትገነባው የጦር ቤዝ እየተነሳች የቀጠናው ዘብ በመሆን ምዕራባውያንን ታገለግላለች። እንደወረደ ሲገለጽ ደግሞ፣ ወታደር በርካሽ ዋጋ እያመረተች አገልግሎታቸውንና ህይወታቸውን በዶላር ለምዕራባውያን ትቸበችባለች። ይህ የሚፈጥረውን እድል ሲረዱ ጄነራሎቿ ቢዝነስማን ይሆኑና እንደነ ዋግነር ግሩፕስ አይነት መርሰናሪ (ቅጥረኛ) ሰራዊት ገንብተው ሀብት በማካበት አለም ይጠመዳሉ።

User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

ቱርክ ከሶማሊያ ጋር አዲስ ወታደራዊ ስምምነት ፈጸመች። ስምምነቱ ሶማሊያ ወታደራዊ አቅሟን እንድትገነባ በቁስና በስልጠና ከማገዝ አንስቶ እስከ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች (ድሮኖችን ጨምሮ) በሽያጭ ማቅረብን ያካትታል። በዚህ መልክ ቱርክ በሶማሊያ ያላትን ጥቅምና ጂኦፖለቲካዊ ሚና ከማስጠበቅም በላይ ተጽእኖ ፈጣሪነቷን ትጨምራለች። ከተበታተነ የጎሳ ፖለቲካዋ የምትወጣበትን እድል ያገኘችው ሶማሊያም፣ በአረብ አገራት ትብብርና እርዳታ ጠንካራ አገረመንግስት ወደ መምራት እየተሸጋገረች ይመስላል። እስካሁን በዲፕሎማሲው ረገድ ብዙዎችን ከጎኗ ማሰለፍ ችላለች። ይህ ሁለት እንደምታዎች አሉት። በየመን ታጣቂያን ላይ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰዱ ያሉ ምዕራባውያን በኢንግሊዞች ተነሳሽነት ለሶማሊላንድ እውቅና ሰጥተው በበርበራ የኢትዮጵያ የጦር ቤዝ ግንባታ ካፋጠኑት፣ በተቀናቃኝ ጎራ ማለትም በአረቦች የምትታገዘው ሶማሊያ በቀጥታ ጦርነት ለመክፈት ትችላለች። ነገርዬው የሁለት አገራት ጉዳይ ሳይሆን ብዙ አገራትን ከጀርባው ያካተተ ዓለም ዓቀፋዊ የፕሮክሲ ግጭት ነው የሚሆነው። ሁለተኛው እንደምታ ጉዳዩ ወደ ከፋ ምስቅልቅል ሊያመራ እንደሚችል ተገንዝበው ምዕራባውያኑ ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠታቸውን ካዘገዩ፣ የኢትዮጵያ የወደብ ውል ከወረቀትና ከሰሞንኛ ጫጫታ ሳያልፍ ይቀራል። በዛም አለ በዚህ፣ የበርበራ ወደብ ከጥቅሙ ይልቅ ኢትዮጵያ አይታው የማታውቅ ጦስ ይዞበታ እንደሚመጣ ሳይታለም የተፈታ ሆኗል። በእንጭጭ መሪ የምትታመሰው አገር መከራዋ በዝቷል።

በነገራችን ላይ አዲስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሆነው የተሾሙት የትዊተሩ አምባሳደርም፣ ግልፍተኛነታቸውን ለታዘበ ሁኔታዎችን እንደሚያባብሱ ይገመታል።

Image
The Horn of Africa with notable Turkish projects in dashed red boxes, and key port agreements and military bases of other powers in blue (Clingendael Institute, May 2019).

User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

የብልጽግና መንግስት የአፍሪካን ህብረት የድራማ ማዕክል አድርጎት ሰንብቷል። የሶማሊያ ፕሬዝደንት ተፈጸመብኝ ያሉት የሰውዬውንና የሚወክሉትን አገርና ህዝብ ክብር የሚገፍ ድርጊት እውነት ከሆነ፣ በሁለቱ አገራት ያለውን ውጥረት የሚያባብስ ድርጊት ነው። ወደ ግጭት የሚያመራበት እድል ጨምሯል። አምባገነኖች ከአገር ጉዳይ ይልቅ የግል ጉዳይ ስስ ብልታቸው ነው፣ በቀላሉ ጉልበት ወደ መጠቀም ያመራቸዋል። በአገር ውስጥና ውጭ ፈተናዎች የበዙባት አገር (በብልጽግና ሰዎችም የማይካድና የተባለ ሀቅ ነው) መጨረሻዋ እየተቃረበ ይመስላል።

Post Reply