ግብጽ እንደ ሊብያ

CURRENT AFFAIRS IN ETHIOPIA AND THE REGION


Post Reply
User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

ጋዳፊ ከመሞቱ ከአንድ ወይም ሁለት አመታት በፊት አፍሪካውያን የሚገበያዩበት አዲስ ገንዘብ እያሳተመ ነበር። በአፍሪካ ህብረት ይፋ አደረገው። አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት መሪዎች የጉዳዩን ክብደት በቅጡ የተረዱት አይመስሉም ነበር። ምዕራባውያን ባንከሮችና መንግስቶቻቸው ግን በአይናቸው የመጣባቸው ያክል ነበር ያመረሩት። ብዙም አልቆዩም ዓማጺያኖችን አስታጥቀው ሲቪል ዋር በመፍጠር ከጥቂት ወራት ብኋላ በኔቶ አማካኝነት ቀጥቅጠው ከስልጣን አስወገዱት።

ዛሬ ግብጽ ልክ የብሪክስ አባል በሆነች ማግስት፣ በዶላር ላለመገበያየት ወስናለች የሚል ዜና እየተሰማ ነው። የዜናው እውነተኛነት አጠራጣሪ ቢሆንም ሲሲ አያደርገውም አይባልም። ታድያ ይህ የግብጽ ውሳኔ እንደ ሊብያው የምዕራባውያን ባንከሮችን እንጀራ የሚፈታተን ባይሆንም፣ ለሌሎች አገራት መጥፎ አርአያና ተነሳሽነት ስለሚሆን፣ እውነት ከሆነ በቅርቡ እርምጃዎች ሲወሰዱ መመልከታችን አይቀርም። በቅድሚያ ከእስራኤል ቀጥሎ ከፍተኛ ወታደራዊ ድጋፍ (military aid) ከአሜሪካ በማግኘት የምትታወቀው ግብጽ፣ ይህን ጥቅም በማስቀረት ወይም ለማስቀረት በማስፈራራት አመሏን እንድታሳምር ያስገድዷታል። ያ አልሰራ ካለ ሲሲ ይከረበታል። ይህ ውሳኔ ከሲሲና ካቢኔው ባለፈ ሰፋ ያለ ድጋፍ ያለው ከሆነ ደግሞ ግብጽ እንደ ሊብያ አመድ የምትሆንበት እድል አለ። በቀጠናው ካለው ትርምስ አንጻር ውጥረቶች መቋጫቸው ግጭት ይመስላል።

Post Reply