China in Ethiopia

ECONOMICS, POLITICAL SCIENCE, SOCIOLOGY, ...


Post Reply
User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

Over 100 Ethiopian students win Chinese scholarships

A total of 143 Ethiopian university students have won scholarships provided by the Chinese government to help them pursue graduate and post-graduate studies across different academic fields in the country's largest Addis Ababa University (AAU).

Speaking at the awards ceremony of the China-Ethiopia Friendship Scholarship on Friday at the AAU, the university's Interim President Samuel Kifle said the Chinese government and different universities in China have had "strong and meaningful collaboration with the AAU, which helped us to train our faculties, to train our students."

He said the collaboration between Chinese and Ethiopian academic institutions is reflected in the robust Sino-Ethiopia ties.

Chinese Ambassador to Ethiopia Zhao Zhiyuan for his part called on the scholarship recipients to help contribute to Ethiopia's socioeconomic development.

Noting that the AAU and its graduates have over the years played an important role in fostering China-Ethiopia ties, the ambassador underscored the need to further strengthen the AAU's role as a "bridge" between the two countries.

Mulugeta Ayele, one of the scholarship recipients, said the opportunity will help him and his fellow students to further their studies and, eventually, contribute to Ethiopia's development.

The scholarship awards ceremony also featured an awards ceremony for 22 Ethiopian students who had won the "Chinese Bridge" language proficiency competition.

China.Org

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

"ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና ነው - አምባሳደር መለስ ዓለም" ኢዜአ :lol:

ቻይና "አንድ ቻይና" የሚል ፖሊሲ ታራምዳለች። ታይዋን፣ ሆንግኮንግ ምናምን የሚባሉ ግዛቶች የቻይና ሉኣላዊ ግዛቶች ናቸው ማለቷ ነው። ሆንግኮንግን ከሞላ ገደል ጨብጣታላች። ታይዋን ትቀራለች። ታይዋን እንደ ሆንግኮንግ ቀላል አትሆንም። አንዱና ዋነኛ ምክንያት አሜሪካ የጦር ቤዝ በታይዋን ስላላት ነው። በተጨማሪም ታይዋን በነጻ ገበያ ስርዓት የምትመራ እንደ ጅምር ዴሞክራቲክ አገር ትታያለችና ይህን ርዕዮተ አለም በሚያቀነቅኑና ቻይናን እንደ ስጋት በሚያዩ ምዕራባውያን ድጋፍ ታገኛለች። እንደ ኢትዮጵያ ያለች ድሃና ዘርፈ ብዙ የውስጥ ችግር ያለባት አገር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ለዘብተኛ መሆን ይጠበቅበታል። በተለይ ደግሞ እንደህ አይነት የሚፋጅ የርዕዮተ አለምና የጂኦፖለቲካ ውጥረት ያለበት ጉዳይ ሳይድ መያዝ አስፈላጊም ትክክልም አይሆንም።

የብልጽግና መንግስት የሚያራምደው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ልክ እንደ መሪው ግራ የገባው ነው። አብይ አሕመድ ሙትት ያለ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንደሚያራምድ በመደመር መጽሃፉ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል። የኢትዮጵያን ጥቅም ማስቀደም አንችልም። የነሱን ጥቅም ማስቀደም አለብን። ድሃ አገር ሉኣላዊነት የለውም። ወዘተ። የዛ ነጸብራቅ ደሞ እዚህ ላይ እያየነው ነው።

ቻይና የአንድ ቻይናን ፖሊሲ ስለምታራምድ፣ ለአገሯ አንድነትና ሉኣላዊነት የምትቆረቆረውን ያክል ለሌሎች አገራት አንድነትና ሉኣላዊነት እንደምትቆረቆር ማሳየት ይጠበቅባታል። አለበለዚያ ሂፖክራት ያስብላታል። ሂፖክራሲ ደግሞ ተቀናቃኞቿን እያከሰረ ያለ ጉዳይ ነው።

ለምሳሌ በሊብያ የእርስ በእርስ ጦርነት ግዜ ጋዳፊና አማጽያኖቹ ሲጋጩ፣ ወደ ሶስት መቶ ሺ የሚገመት ሲቪል ከቀየው ተፈናቅሏል በርካቶች ሞተዋል በማለት፤ የሲቪልያን ህይወት መታደግ አለብን በሚል ሰበብ (በወቅቱ በአፍሪካ ህብረት የተቋቋመን አሸማጋይ ኮሚቴ ከመንገድ በመመለስ) ጋዳፊ ላይ በኔቶ ጣምራ ጥቃት ሊብያን አውድመዋታል። ሊብያ ለሁለቱም ወገን (ለጋዳፊ ደጋፊዎችም ለአማጻያኖቹ ደጋፊዎች) ሳትሆን ቀረች። ንብረትና ሃብቷ ተዘርፎ የአሸባሪዎችና የማፊያዎች ማእከል ሆነች። በአንጻሩ ደግሞ ከሁለት ሚልዮን ህዝብ በላይ በተፈናቀለበትና ከግማሽ ሚልዮን ህዝብ በላይ ህይወቱን ባጣበት የትግራይ ጦርነት ጠንከር ያለ መግለጫ ለማውጣት እንኳን ተቸግረው ከሁለት አመታት በላይ ዘልቀው አይተናቸዋል። የአብይ አሕመድ የፕራይቬታይዜሽን ፖሊሲን በጉጉት ሲጠባበቁ። ከትግራዩ ጦርነት ባስ ሲል ደግሞ በጋዛ አየናቸው። ወደ 2 ሚልዮን የሚገመት ህዝብ ሲፈናቀልና ከ20ሺ በላይ የሚሆን ሲሞቱ፣ በጋዳፊ ላይ የወሰዱት አይነት እርምጃ በኔታንያሁ ላይ ሊወስዱ ይቅርና ጭራሽ ትጥቅና ስንቅ ሲያቀበሉ፣ ሲያስተባበሉ፣ ከህግ ተጠያቂነት ለመካለከል ሲሞከሩ ይታያሉ። ለራሳቸው አልቀረላቸውም በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪነት በአለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ክስ እየተመሰረተባቸው ይገኛል።

ይህ አይነቱ ኢንኮንሲስተንሲና የግል ጥቅምን ብቻ በማስቀደም የታወረ አቋማቸው ለዘርፈ ብዙ ኪሳራ እየዳረጋቸው መሆኑን ቻይና ትገነዘባለች። ቻይናና ሌሎች ተቀናቃኝ ሃያላን አገራት በዚህ የምዕራባውያን የፖለቲካ ኪሳራ ካፒታላይዝ እያደረጉ ይገኛሉ። በመሆኑም ቻይና ወጥ አቋም የማራመድ "ግዴታ" አለባት፤ ተሽላ ለመታየት። ለዚህም ነው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግኑኝነት ምንም ይሁን ምን፣ በሶማሊያ አንድነትና ሉኣላዊነት የምታምን መሆኑን በግልጽ ያሳወቀችው።

ይህም ማለት ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የገባችውን ውል አትቀበልም ማለት ነው። ባስ ብሎም ኢትዮጵያ የሶማሊያን አንድነትና ሉኣላዊነት እንድታከብር ጠይቃለች። ግድ ነዋ። አንድ ቻይና እያለች እንዴት ሁለት ሶማሊያ ልትል ትችላለች?

ታድያ እንደ አገር የኢትዮጵያ አቋም ምን መሆን ነበረበት? ቻይና የኢትዮጵያን "ጥቅም" የሚጻረር አቋም ስታራምድ፣ ኢትዮጵያ የለም እኔ የቻይና አንድ ፖሊሲን እደግፋለሁ የሶማሊያ አንድነትን ግን እጻረራለሁ የሚል አቋም ነው በግልጽ ማራመድ ያለባት? በተለያዩ ግዜያት የተገለጡ አቋሞች ቢሆኑም ይህ ተብሏል። ለሶማሊላንድ እውቅና እንሰጣለን የወደብ ስምምነቱ አካላ ነው። የቻይና አንድ ፖሊሲ እንደግፋለን ይኸው በይፋ ተብሏል። ምን ማለት ነው? ምን አይነት ግራ መጋባት ነው?

በራስ ጥቅም የሚቃኝ ፖሊሲ እኮ እንደ ቻይና ኮንሲስተን መሆን ይችላል። ለምሳሌ የባህር በር ለማግኘት ሲባል ሶማሊላንድን እውቅና መስጠት አስፈላጊ ከሆነ፣ ለህዝቦች የነጻነት አስፓይሬሽን ግድ እንደሚሰጠው አካል መስለህ በመቅረብ፣ የቻይናን አንድ ፖሊሲ መደገፍም ማውገዝም ሳይጠበቅብህ በዝምታ ማለፍ ትችላለህ። ዝምታ ለትርጉም ጥሩ ነው። አማርኛ እንዳበጁሽ ከሚባለው በላይ ነው፣ ዝምታ እንዳበጁት ነው የሚተረጎመው።

ነገር ግን ግራ የገባው በአብይ አሕመድ የመደመር መጽሓፍ የሚመራው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለራስ ክብር የሌለው ሸፋዳ አቋም አራመደ። ቻይንዬ ምንም እንኳን ከኔ ጥቅም በተቃራኒ ብትቆሚም እኔ ላንቺ አንድ ቻይና ፖሊሲ ከሌሎች ጋር ለመናቆር ዝግጁ ነኝ። ነገር ግን ስለ ሶማሊያ አንድነት አትጠይቂኝ። ላንቺ አገር አንድነት የሰጠሁት ድጋፍ ይበቃል። አቋሜ ወጥ ባይሆንም ግድ የለኝም፣ ብቻ ትንሽ ልኑርበት። ብድር በመልቀቅ፣ እዳ በመሰረዝ፣ ወዘተ ተባበሪኝ። .... :lol:

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Baykedagn
Posts: 13
Joined: Sun Sep 03, 2017 6:39 pm

ጥሩ እይታ ነው። ነገር ግን የቀድሞ ኢትዮጵያ መንግስታት ያራምዱት የነበረ አቋም ነው። አሁን ያንን አቋም መቀየር ሌላ ፈተና ውስጥ መግባት አይሆንም? ቻይና እንደሆነ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማንቁርት በእድ ቀፍድዳ ይዛዋለች። እንዴት በዚህ ሰዓት ከቻይና ጋር የሚያፋጥጣቸውን አቋም ሊያራምዱ ይችላሉ?

"Reason has always existed but not always in a reasonable form." KM
User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

ዝም ማለት ይችሉ ነበር እኮ ነው ዋናው ነጥብ። አቋማቸውን በይፋ መግለጽ አይጠበቅባቸውም ነበር። ማን ግድ አላቸው። ከዛ ብኋላ ዝምታቸውን የፈለገ ሰው እንደፈለገ ይተርጉመው።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

China's Belt and Road Initiative (BRI), evolving to become the overarching framework through which China engages with the continent, has seen billions pumped into developing projects such as Ethiopia’s Eastern Industrial Zone (EIZ) – described by the country’s former Prime Minister, Meles Zenawi, as an example of China’s “irreplaceable role” in the Ethiopian economy. The zone is 100% owned and managed by China’s Qiyuan Group.

Reports of corruption are widespread. Working conditions are under increasing scrutiny. Similar projects have been investigated for using special economic zones to side-step U.S. import tariffs. Nevertheless, so long as Chinese investment appears lucrative (and the EIZ has created more than 20,000 new jobs), China will continue to attract nations such as Ethiopia.

The consequence is that Afro-Chinese relations run the risk of becoming dangerously asymmetrical.

Many in the West see China’s investment as a ‘soft’ means of establishing itself globally. Some even suggest that through projects such as the EIZ, Ethiopia (and elsewhere) may become Chinese “colonies”. This is certainly hyperbole. From Ethiopia’s perspective, claims of “Chinese neo-colonialism” come from “fear in the West of growing [Chinese] influence in Africa”. Often, investment stems from socioeconomic weaknesses back home, with many Chinese workers seeking greater financial opportunities building roads etc.

For many African nations, Chinese loans appear more conducive to longer-term development. Moreover, unlike the IMF’s, they aren’t conditional on reform – a selling-point Xi Jinping emphasises. “We have a high degree of agency,” Ethiopia’s deputy economic commissioner has been quoted as saying, “yet Western countries try and advise us about what our…law should be.”

Hidden Content
This board requires you to be registered and logged-in to view hidden content.

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

Closure of Chinese Factories in Ethiopia Amid Tax Disputes

The Ontex factory in Ethiopia, once a bustling hub producing 400,000 diapers per hour, has ceased operations due to prolonged tax disputes with the government, as reported by the China Global South Project. This closure is indicative of the worsening business environment in the country.

Despite the International Monetary Fund (IMF) forecasting a 6.2% growth for the Ethiopian economy this year—a notable achievement for a nation recovering from a significant debt crisis and a two-year civil war—the government faces the challenge of fostering private sector growth, especially in the manufacturing sector, to meet these growth targets.

Separately, the Chinese embassy in Addis Ababa has expressed its discontent with a report by CGSP last week, which highlighted concerns about Chinese investment in Ethiopia. The embassy aims to clarify misconceptions and set the record straight regarding Chinese involvement in the country, underscoring the need for accurate representation of its investment landscape.

Desclaimer: CGSP retracted its report on the strong press statement from Chinese embassy in Addis Ababa. :?

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

Belt and Road Initiative ከተመሰረተ ወዲህ አንድ የተለመደ ቃል አለ የቻይናን የውጭ ጉዳይ ስልት የሚገልጽ Debt-Trap Diplomacy ይሰኛል። አገራት መክፈል ከሚችሉት በላይ ቻይና ብድር ትሰጣለች። መክፈል ሲያቅታቸው የምትፈልገውን ነገር እንዲሰጧት ወይም እንዲያደርጉ ትጠይቃለች። አሪፍ ወጥመድ ነው። አገራት አልኩ እንጂ አምባገነኖች ናቸው ዋናው ዒላማ፣ የህዝብ ተጠያቂነት የሌላቸው፣ ለስልጣናቸው ሲሉ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ የማይሉ። ከነዚህ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት። ቻይና ከነ ስዩም መስፍን ጋርም ሆነ ከነ አብይ አሕመድ ጋር ለመስራት ምንም አትቸገረችም። ያኔም ዛሬም ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ብድር ባሰኛቸው ጊዜ ምንም ሳታወላውል ትሰጣቸዋለች። ትላንትም ዛሬም መክፈል የማይችሉትን ብድር ቆልለዋል። በነቀዘ ስንዴና ኤክስፓየርድ ባደረገ የምግብ ዘይት ዲፕሎማሲያቸውን ሲከኩ ለነበሩ ምዕራባውያን ይህ የቻይና ስልት ፈታኝ ሆኖባቸዋል። ቻይና ለረዥም ጊዜያት በአገራት ፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ ያለመግባት ስትራቴጂ ስትከተል ነበር። ዛሬም ቢሆን ስለታይዋን ያለህን አቋም ካሳመርክ ምንም አትልህም። ይህ ለአምባገነኖች ሲሳይ ነው። በተለይ ደግሞ አንዳንድ የሚታዩና የሚዳሰሱ የልማት ስራዎችን ስለምትሰራ ለፕሮፓጋንዳ አመቺ ነው።

የአፍሪካ አገራት በቅኝ ከተገዙበት ዘመን አስንቶ እስከቅርብ ግዜ ድረስ በበላይነት አህጉሩን ስትቆጣጠሩት ነበር፣ ነገር ግን ከነቀዘ ስንዴያችሁና ምጽወታችሁ ውጪ ምን የሚታይ ስራ ሰራችሁ ተብለው ሲጠየቁ ምዕራባውያን ለመመለስ ይቸገራሉ። ድልድይ፣ መንገድ፣ የሰሩበት ስፍራ የለም። በእርዳታም ሆነ በብድር ከሚሰጧት እያንዳንዷ ዶላር ጀርባ፣ የሆነ ፕሪኮንዲሽን ያስቀምጣሉ። ይህን አድርግ፣ ይህን አታድርግ፣ በዚህ ግባ፣ በዚህ ውጣ። አምባገነኖች ለስልጣናቸው ጠንቅ እስካልሆነ ድረስ ችግር የለባቸውም። አድርጉ የተባሉትን ያደርጋሉ። ለስልጣናቸው ጠንቅ መስሎ በታያቸው ግዜ አሻፈረኝ ይላሉ። አሻፈረኝ ባሉ ማግስት ተመንግለው ይጣላሉ። እነሱን ተክተው የሚፈለፈሉ አምባገነኖች ከተመሳሳይ እጣፈንታ ቻይና እየታደገቻቸው ነው። ከምዕራባውያን ጋር በተኳረፉ ቁጥር ፊታቸውን ወደ ቻይናና ራሺያ ያዞራሉ። እንደነ ኢትዮጵያ ያሉ ጂኦፖለቲካሊ ቁልፍ የሆኑ አገራት ይችን ዥዋዥዌ መጫወት ሲጀምሩ (ሲያቆላምጧት ዴሊኬት ባላንስ ይሏታል) ለምዕራባውያን ራስ ምታታቸው ግብዳ ይሆናል። ቻይና የበለጠ ታበድራለች፣ እርዳታ ትሰጣለች፣ ዲፖሎማሲያዊ ድጋፍ ታደርጋለች። ዒላማዋን ግን ፈጽሞ አትስትም። ኢኮኖሚውን ቀስ በቀስ ትቆጣጠረዋለች። መውጫ በሌለው የብድር አረንቋ ውስጥ አገራቱን ከትታ፣ ፍላጎቷን ታስፈጽማለች። ፍላጎቷ ዲሞክራሲ ሰብአዊ መብት ምናምን የሚሉ ንትርኮች የሉትም፣ ኢኮኖሚክ ሪተርኑን ብቻ ነው የምታሰላው። እንደምዕራባውያን መንግስታት መሪዎቿ ህዝባዊ ተጠያቂነት የላቸውም። ለምታደርገው ድጋፍና ለምትሰጠው ብድር ማንም ቻይናዊ (ግለሰብ፣ ተቋም ሆነ ቡድን) ለምን ብሎ አይጠይቃትም። ይህ ለቻይናም አማራጭ ለሆነችላቸው አምባገነኖችም ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።

ሰሞኑን የአገራቸውን አዲስ አመት አስመልክቶ በቻይና ኢምባሲ የተዘጋጀ ፌስቲቫል ነበር። የማርሻል አርትና አክሮባት በታከለበት ትእይን የብልጽግና ሰዎች ተገኝተዋል። ከነ IMF እና World Bank (የእናት መቀነት) ጭቅጭቅ ይታደገን ይሆናል ብለው ብልጌዎች የBRICS አባል ሀገራትን በይፋ ከተቀላቀሉ ወዲህ ቻይና ግኑኝነቷን በተጠናከረ መልኩ እንደምትቀጥል ገልጻለች። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ከምዕራባውያን የበለጠ እንደሚነጥላትና ከባባድ ተግዳራቶች እንደሚያጋጥሟት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ይገምታሉ። ከምዕራቡ ራሷን እያገለለች፣ በቻይና መዳፍ ለመጨበጥ እየተቻኮለች ያለችው አገር፣ መጨረሻዋ ምን እንደሚሆን ማየት ነው እንግዲህ። የብልጌ ተቀናቃኞች እዚህ ላይ እንደሚሰሩበት ይገመታል።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

Post Reply