በሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ የጂሃድ ጥሪ አወጁ?

CURRENT AFFAIRS IN ETHIOPIA AND THE REGION



Topic author
dan
Posts: 20
Joined: Mon Apr 13, 2020 11:52 pm

ለዘገባ የሚሆን ፍንጭ ሰጠኋችሁ በለኝ :D

gebetaforum wrote: Fri Jan 12, 2024 5:07 pm

የዚህን ዜና እውነተኛነት ለማረጋገጥ ስንበረብር፣ የአልሸባብ ቃል አቀባይ ከ10 ቀናት በፊት ይህን ጥሪ ማድረጋቸውን የሚጠቁም መረጃ አገኘን። ለጊዜው በየትኛው ሚድያ ይህን ጥሪ እንዳስተላለፉ ለማወቅ አልቻልንም። ይዘቱን እዚህ ላይ ለጥፈነዋል።

የወደብ ስምምነቱ የፈጠረው ውጥረት አልሸባብን የሚያጠናክር መሆኑን የገመተው ጽሁፍ፣ ብዙም ሳይቆይ ከሳምንት ብኋላ አል ሸባብ የተመድ ሄልኮፕተር ጠልፏል። በውስጧ የነበሩ ሰዎች እስካሁን የት እንዳሉ አልታወቀም። ፖሊስ አሰሳውን እንደቀጠለ ነው።
ጽሁፉ አልሸባብ ኢትዮጵያን እንደ እስራኤል እንደሚመለከታት ይገልጻል። እስራኤል ቀስ በቀስ ፍልስጤምን እንደሰለቀጠቻት ሁሉ የኢትዮጵያም ፍላጎት ሶማሊያን መሰልቀጥ ነው ይላል። ስለሆነም ለጅሀድ ተነሱ የሚል ጥሪ ማስተላለፉ ታውቋል።

ይህ አይነት ጥሪ በአልሸባብ ሁሌም ሲባል የኖረ እንደመሆኑ መጠን ብዙም ትኩረት ላንሰጠው እንችላለን። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍልና ቀውስ እንዲህውም ሶማሊያ ላይ እየተፈጠረ ያለው ናሽናሊስቲክ እንቅስቃሴ ተዳብለው ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት መሰንዘር አይችሉም ብሎ መገመት ያስቸግራል።

Post Reply