86ቱ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስም ዝርዝር

FACTS ABOUT ETHIOPIA AND THE REGION


Post Reply
User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

  1. ኦሮሞ
  2. አማራ
  3. ሶማሌ
  4. ትግራይ
  5. አፋር
  6. ሲዳማ
  7. አገው
  8. ዎላይታ
  9. ከምባታ
  10. ሀዲያ
  11. ጋሞ
  12. ጉራጌ
  13. ኢሮብ
  14. አርጎባ
  15. ቱለማ
  16. ስልጤ
  17. ሺናሻ
  18. አኝዋክ
  19. ኑዌር
  20. ሀመር
  21. ኩናማ
  22. ጉምዝ
  23. በርታ
  24. በና
  25. አሪ
  26. ሙርሲ
  27. ቡሜ
  28. ካሮ
  29. ፀማይ
  30. ኮንሶ
  31. ዳሰነች
  32. ቦረና
  33. ገርባ
  34. አላባ
  35. አርቦሬ
  36. ባጫ
  37. ቤንች
  38. ባስኬቶ
  39. ቡርጂ
  40. ጫራ
  41. ጋዋዳ
  42. ጌዲኦ
  43. ጊዶሌ
  44. ጎፋ
  45. አደሬ
  46. ከፊቾ
  47. ኮንታ
  48. ኒያንጋቶም
  49. ናኦ
  50. ቀቤና
  51. ሱርማ
  52. ጠንባሮ
  53. የም
  54. ወርጂ
  55. ዲዚ
  56. ዶንጋ
  57. ዳውሮ
  58. ዲሜ
  59. ምዓን
  60. ኮሞ
  61. ማረቆ
  62. ሞስዬ
  63. ኦይዳ
  64. ቦዲ
  65. ፈዳሼ
  66. ኮሬ
  67. ማሌ
  68. ማኦ
  69. መሰንጎ
  70. መዠንገር
  71. ቀዋማ
  72. ቀጨም
  73. ሸኮ
  74. ዘየሴ
  75. ዘልማም
  76. ሽታ
  77. ቤተ እስራኤል
  78. ማሾላ
  79. ኮጉ
  80. ድራሼ
  81. ገባቶ
  82. ጌዲቾ
  83. ብራይሌ
  84. ሙርሌ
  85. ኮንቶማ

ምንጭ - የኢትዮጵያ ታሪክ

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋዎች ስም ዝርዝር

User avatar

Kitaw
Posts: 22
Joined: Sun Sep 03, 2017 6:09 pm

ሙርሲ

✬✬✬

.
ሙርሲ በባህላዊ ቅርሶቻቸው ከሚታወቁት የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ልዩ እና ማራኪ ብሔሮች አንዱ ነው። ስለ ሙርሲ ህዝብ አንዳንድ አስደናቂ እውነታዎች እነሆ፥

ሙርሲዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በኦሞ ወንዝ የታችኛው ሸለቆ አካባቢ ይኖራሉ። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ለሱዳን ድንበር ቅርብ የሆነ ክልል ይኖራሉ።

ልዩ ከሆኑት የሙርሲዎች ባህላዊ ልማዶች ሴቶች የታችኛውን ከንፈራቸው በጥተው የሚያንጠለጥሉት የሸክላ ማጌጫ ነው። ይህ ልማድ ቀስ በቀስ የታችኛውን ከንፈር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመዘርጋት ሸክላ ወይም የእንጨት ሳህኖችን ማስገባትን ያካትታል። ይህም የውበት እና የብስለት ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል።

ሙርሲዎች በሚደንቁ የሰውነት ሥዕሎች እና ንቅሳቶች ይታወቃሉ። በሰውነታቸው ላይ ውስብስብ ንድፎችን ለመፍጠር እንደ ሸክላ እና በአካባቢው የሚገኙ የተፈጥሮ ማዕድናትን ይጠቀማሉ። ይህም የውበት እና ባህል መገለጫ ሆኖ ያገለግላል።

ከፊል አርብቶ አደር ከፊል አርሶ አደር ለሆኑት ሙርሲዎች ከብቶች በኑሯቸው ውስጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። ከብቶች የምግብ ምንጭ ብቻ ሳይሆን የሀብት እና የማዕረግ ምልክት ናቸው። በሰርግ እና ሌሎች ማህበራዊ ግብይቶች ግዜ እንደ መገበያያ ሆነውም ያገለግላሉ።

ሙርሲዎች በኦሞ ወንዝ ዳርቻ ጎርፍ በመከንተር ግብርናን ይለማመዳሉ። እንደ ማሽላ እና በቆሎ ያሉ ሰብሎችን ያመርታሉ። ግብርናቸው ከወንዙ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመከንተር ሁኔታ ጋር የተቀናጀ ነው።

ሙርሲዎች የትልቅ ሱርሚክ ቋንቋ ቡድን አካል የሆነውን ሙርሲ የሚባል የኒሎ-ሳሃራን ቋንቋ ይናገራሉ። ቋንቋቸው የባህላዊ ማንነታቸው ዋና አካል ነው።

ባህላዊ እምነቶች እና ልምዶች በሙርሲ ህይወት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። የባህላዊ እምነት ተከታዮች ሲሆኑ፣ አምላካቸው አንዳንዴ በቀስተ ዳመና የሚገለጥ በሰማይ የሚኖር ሲሆን ቱሚ ብለው ይጠሩታል። ከመንፈሳዊነታቸው ጋር የተቆራኙ የተለያዩ የአምልኮ ሥርዓቶች እና ልምዶች አሏቸው።

ላለፉት ሃያ ዓመታት ገደማ የሙርሲ ብሔረሰቦች ኢትዮጵያን ለሚጎበኙ ቱሪስቶች፣ የቱሪስት መስህብ ሆነው ቆይተዋል። ይህም በማህበረሰባቸውና አካባቢያቸው ውስጥ የተለያዩ አወንታዊና አሉታዊ ለውጦችን አስከትሏል።

የሙርሲ ልዩ የአኗኗር ዘይቤ እና ባህላዊ ልምምዶች ለአንትሮፖሎጂስቶች እና ለቱሪስቶች ትኩረት የሚስቡ ርዕሰ ጉዳዮች ሆነዋል።

ምንጭ

Hidden Content
This board requires you to be registered and logged-in to view hidden content.
Post Reply