ስለ ኮሮና ቫይረስና ኮቪድ-19 በሽታ

Post Reply

Topic author
alisheikh76
Posts: 1
Joined: Tue Mar 31, 2020 3:16 am

ቫይረስ ምንድ ነው?
``````````````````````
By: Alisheikh A Adem

ቫይረስ በዓይን ከማይታዩ እጅግ አነስተኛ ጥገኛ ፍጥረት ይመደባል።
ቫይረስ በሂይወትና ሂይወት በሌለው የሚመደብ ሁኖ ሂይወት ባለው ነገር ላይ ሲያርፍ ሂይወት የሚዘራና ሂይወት በሌለው ነገር በሚያርፍበት ግዜ ደግሞ ሂይወት-አልባ ኹኖ፡

1. ናሃስ ላይ.................... 4 ሳዓት
2. ካርቶን (ወረቀት). ...... 24 ሳዓት
3. ብረት (steel)........... 72 ሳዓት
4. ፕላስቲክ. ................. 72 ሳዓት
5. መስታዉት. ............... 96 ሳዓት መቆየት ይችላል።

የቫይረስ ዓይነቶች:

1) አር ኤን ኤ (RNA)
2) ዲ ኤን ኤ (DNA)

የኮሮኖ ቫይረስ ምድቦች:

1) አልፋ
2) ቤታ
3) ጋማ እና
4) ዴልታ

ከቤታ ምድብ ኮሮና ቫይረሶች፡

1. SARS-COV
2. MERS-COV
3. SARS-COV-2 ናቸው::

SARS-COV-2 አር ኤን ኤ ቫይረስ ሞሎኲል ኹኖ 30 ሺ መሰረታዊ ዘር (bases) እና 15 ዘር (gene) አለው። የኮሮና በሽታ አምጪ ቫይረስ #SARS_COV_2 ይባላል። በሽታው ደግሞ ኮቪድ-19 ተብሎ ይጠራል። ይህ በሽታና ቫይረስ በቻይና ሁቤ ክ/ሃገር ዉሃን ከተማ ታህሳሥ 2019 ዓ/ም ለመጀመርያ ግዜ ታየ።

ቫይረስ እንዴት ይራባል?
``````````````````````````
ቫይረሶች ሂወት ባለው አካል ሲያርፉ በቀጥታ ወደ ሴል ገብቶ የሴሉን ንኲሊያስ በመቆጣጠር የራሱ አማሳያ እንዲተካ ትእዛዝ ያስተላልፋል። በዚህ የማራባት ግዜ የዘሩ (DNA OR RNA) ለአምሳያው ኮፒ በሚያደርግበት ወቅት በሚፈጠር ስህተት አዲስ ቫይረስ ሊፈጠር ይችላል። ይህ አዲስ ቫይረስ ከበፊቱ ቫይረስ የተሻለ፥ ተመሳሳይ ወይን አደገኛ አዲስ በሽታ አምጪ ሁኖ ሊፈጠር የሚችልበት አጋጣሚ አለ።

√ ኮሮና ቫይረስ #COVID-19 በሽታ አምጪ ልክ እንደ ከዚህ በፊቱ የተፈጠሩ ገዳይ ቫይረሶች በዘር ኮፒ ስህተት የሚፈጠሩ ቫይረሶች አንዱ ያደርገዋል። የሰው ልጅ አሁን የደረስበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ዘረ-ህንድስና (genetic engineering) አዳዲስ ቫይረስ፥ ባክተርያ፥ ፈንገስ እና ተዛማጅ ነገሮች በቤተ-ሙከራ መፍጠርና ማሻሻል ከጀመረ ዉሎ አድሯል።

√ ቫይረሶች ለየት የሚያደርጋቸው ከእንሰሳ ወደ ሰው የሚተላለፉ አደገኛ በሽታ አምጪ መኾናቸው ነው። በተለይ የሌሊት ወፍ ኮሮና ቫይረስ ጨምሮ ሌላ 60 የተለያዩ ቫይረሶች ተሽካሚ (host) እንሰሳ ናት።
√ ቫይረሶች ተለዋዋጭ ባህርይ ስላላቸው መድሃኒት ለማግኜት አታካችና እረጅም የሙከራ ግዜ የሚጠይቅ በመኾኑና ከነካቴው ላይገኝለትም ይችላል። ነገር ግን የቫይረሱ ቅሪት ወይንም የተዳከመ ቫይረስ (attenuated virus) ወይንም ተመሳሳይ አርቲፊሻል ኬሚካል በክትባት (vaccine) መልክ ተዘጋጅቶ የሰዉንታችንን የመቋቋም ብቃት (antigen) ቀድሞ እንዲያዘጋጅ በማድረግ በሽታው ለመከላከል ይቻላል። ሰለዚህ የቫይረስ መድሃኒት ለማግኜት ከላይ በተጠቀሱ ምክንያቶች መድሃኒት በአጭር ግዜ ለማግኜት አስቸጋሪ ያደርገዋል።

√ ስለዚህ የተቀናጀ የመከላከል ስራ በመሥራት፡ የግል ንጽህና፥ የህ/ሰብ ንጽህና በመጠበቅ እጆቻችን ቶሎ ቶሎ በማጠብ አፋጣኝ መፍትሄ በመውስደ መከላከል ይቻላል። በተጨማሪም ራስህን ከማህበራዊ ንኪኪ በማግለልም ወይንም በማራቅ እንደ ዋነኛ አምራጭ የመከላከል ሥልት መውሰድም ይቻላል።

እጅን መታጠብ
``````````````````
እጅን መታጠብ እጅግ አስፈላጊ የሚኾንበት ዋነኛው ምክንያት እጅን ብዙ ነገሮችን ሰለሚነካካ ነው። እጃችን ቫይረስ ያለበት ነክቶ ቫይረሱ በነካው እጃችን ኣይናችን፥ ኣፍንጫችንና ኣፋችንን በምንንካካበት ግዜ ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን የመግባት ዕድሉ አሰፋንለት ማለት ነው።
እጃቻንን በዉሃ ብቻ ማጠብ በቂ አይደለም። ከዉሃ በተጨማሪ ማንኛዉም ዓይነት ሳሙና ተጠቅመን ለ 20 ስኮንድ መዳፋችንና የዉጩም እጆቻችንንና ጣቶቻችን በማሸት ቫይረሱን መክላትና መበታተን ይቻላል። አልኮልም (sanitizer of at least 65% alcohol) ተመሳሳይ አገልግሎት በመሥጠት የቫይረሱ ግድግዳ (membrane) በመናድ የቫይረሱ ሞሎኲል ጉዳት-አልባ የማድረግ ከፍተኛ ችሎታ አለው።
√ ኮሮና ቫይረስ በሽታ ሁሉም የህ/ሰብ ክፍል ከህጻን - ኣዋቂና ኣዛውንቶች፡ ነጭ-ጥቁር ሳይል ቦርደር-የለሽ አጥቂ ሰለኾነ ማንም ሰው መዘናጋት የለበትም።

√ ንሮ እንኳን እየሰሩ እንዲሁ ከባድ ቢሆንም ለዚች ክፉ ቀን በቤት ዉሥጥ በመቀመጥ (self-quarantine) እጅግ የተሸለና ብቸኛ አማራጭ ነው (ለቻለ ሰው)። ካልሆነ ግን አልባሌ ቦታ፥ መዝናኛ፥ ባህላዊ፥ ማሕበራዊና ሃይመኖታዊ መስተጋብሮቻችን ለግዜው ወድ ጎን ብንተዋቸው እጅግ አጥብቆ ይመከራል።

ኮሮና ቫይረስ ምናችንን ያጠቃል?
`````````````````````````````````````
ኮሮና ቫይረስ በተለይ የሚያጠቃው የመተንፈሻ አካላችን፡ ከአፍንጫችን እስከ ታችኛው ሳንባችን ሲኾን ከዚህ በተጨማሪም የምግብ መድቀቅያ ሲስተም፥ ልብ፥ ኩላሊት፥ ሆድና የአንጎላችን ስርዓተ-ማእከል የሚያጠቃ ዉስብስብ በሽታ ነው።
User avatar

gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

@alisheikh76 አሪፍ መልዕክት ነው። ነፍስ ዘራህበት ፎረሙን ;)
Post Reply