ኮቪድ19 ጠቃሚ መረጃዎች

User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

We moved the original post to the English topic. Read here.
User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

ከcovid-19 ብሄራዊ የሚንስትሮች ኮሚቴ የተላለፈ ውሳኔ
covid19.jpg
covid19.jpg (92.44 KiB) Viewed 27671 times
User avatar

yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

COVID-19ን አስመልክቶ ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በነጻ መደወል ይቻላል።
.
covid-call.jpg
covid-call.jpg (64.38 KiB) Viewed 27565 times

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

አዲስ አበባ ለምትኖሩ ደግሞ አቅራቢያችሁ ወደሚገኙ ማእከላት በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች መደወል ትችላላችሁ።
.
covid-call-aa.jpg
covid-call-aa.jpg (29.98 KiB) Viewed 27563 times

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

የኮቪድ-19ን ስርጭት ለመግታት ይለግሱ
.
covid19_help.jpg
covid19_help.jpg (64.91 KiB) Viewed 27506 times
User avatar

yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

በታዋቂው የምርምርና የትምህርት ተቋም
Johns Hopkins University ተፅፎ በደረጀ ድረስ የተተረጎመ የኮሮናን ባህሪና መከላከያ የሚገልፅ የምርምር ፅሁፍ ፡፡ :idea:

..
 ቫይረሱ ህይወት ያለው ፍጡር ሳይሆን እራሱን በሚከላከልበት ስስ ስብ የተሸፈነ የፕሮቲን ሞሎኪዩል ሲሆን ወደ አይን፣ አፍንጫ እና አፍ በሚገባ ጊዜ በነርሱ ውስጥ በሚገኝ ክፍተት ውስጥ በመግባትና የራሱን ተፈጥሯዊ ማንነት በመቀየር ወደ ብዙ እና አጥቂ ተውሳክነት ይቀየራል፡፡

 ቫይረሱ ህይወት ያለው ፍጡር ሳይሆን የፕሮቲን ሞሎኪዩል እስከሆነ ድረስ በራሱ ይበሰብሳል እንጂ አይሞትም፡፡ የሚፈራርስበት ጊዜም በአየሩ የሙቀት መጠን፣ የአየሩ እርጥበት መጠን እና ቫይረሱ በተገኘበት ቁስ ይወሰናል፡፡

 ቫይረሱ በጣም ስስ/ ተሰባሪ ሲሆን ከመሰበር የሚከላከው ነገር ቢኖር በዙሪያው የከበበው በጣም ስስ ስብ ነው፡፡ ለዚህም ነው ማንኛውም ሳሙና ወይም የጽዳት መጠበቂያ ቫይረሱን ለመከላከል ፍቱን መፈትሄ የሆነው፡፡ ምክኒያቱም የሳሙናው አረፋ የቫይረሱን ስብ መሰል መሸፈኛ ይሰባብረዋል፡፡ ለዚህም ነው እጃችንን ከ20 ሰከንድ ለማያንስ ጊዜ በደንብ የምናሸው/ ምንፈትገው፡፡ የስብ መሸፈኛውን በሳሙና ስናሟሟው የቫይረሱ የፕሮቲን ሞሎኪውሉል( ዲኤን.ኤ) እራሱ ይበታተን እና ይሰባበራል፡፡

 ሙቀት ስብ መሰል መሸፈኛውን የቀልጠዋል፡፡ ስለዚህ ከ 25 ዲሴ በላይ በሞቀ ውሃ እጃችሁን፣ ልብሳችሁን፣እና ማንኛወንም ነገር እጠቡ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሙቅ ውሃ ሳሙና ብዙ አረፋ እዲያወጣ ስለሚያደርግ የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል፡፡
 አልኮል እና ከ65 እጅ በላይ ከሆነ አልኮል ጋር የተደባለቀ ማኛውም ነገር ማንኛውንም ስብ ያሟሟል በተለይ የቫይረሱን ስስ ስባማ የውጭ ሽፋን ያሟሟዋል፡፡

 ማንኛውም 1 እጅ ቀለም ማስለቀቂያ (Bleach) ( ለምሳሌ በረኪና) ከ 5 እጅ ውሃ ጋር ተደባልቆ የቫይረሱን ስብ ከውስጡ ያሟሟዋል፡፡
 አልኮል ፣ ክሎሪን ወይም ሳሙና ከተጠቀምን በኋላ ሃይድሮጂን ፐርኦክሳይድ (Hydrogen peroxide) መጠቀም የቫይረሱን ዲ.ኤን.ኤ ይሰባረዋል፡፡ ነገርግን ነጹህ ሃይድሮጂን ፐርኦክሳይድ መጠቀም አለባችሁ፡፡ ቆዳን ግን ይጎዳል፡፡

 ቫይረሱ እንደ ባክቴሪያ ህይወት ያለው ነገር ስላይደለ በጸረ ባክቴሪያ ልንገለው አንችልም ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ቶሎቶሎ ልናፈራርሰው ብቻ ነው የምንችለው፡፡

 ማንኛውንም የተጠቀማችሁበትንም ይሁን ያልተጠቀማችሁበትን ልብስ እና አንሶላ በጭራሽ አታራግፉ፡፡ ምክኒያያቱም ክፍተት ባላቸው ነገሮች (አየር እና ውሃ የሚያሳልፉ) ቫየረሱ ሲጣበቅ ምንም መንቀሳቀስ የማይችል ሲሆን በ3 ሰአት ውስጥ እራሱ ይፈራርሳል፡፡ መዳብ በተፈጥሮው ተዋህስያን አምካኝ በመሆኑ እና እንጨት ደግሞ እርጥበትን በሙሉ ስለሚያስወግድ እና አንዴ ቫይረሱ ካረፈበት ስለማይለቀው ቫይረሱ ለ4 ሰአታት ብቻ ተቀምጦበት ይሰባበራል፡፡ ( cardboard ) ላይ 24 ሰአታት፣ ብረታ ብረት ላይ 42 ሰአታት፣ ፕላስቲክ ላይ 72 ሰአታት ከመፈራረሱ በፊት ሊቆ ይችልል፡፡ ነገርግን ካራገፍን ወይም የአቧራ ማራገፊያ ማሽን ከተጠቀምን ቫይረሱ ለቀጣይ 3 ሰአታት በአየር ውስጥ በመቆየት ወደ አፍና አፍንጫችን የመግባት እድል ያገኛል፡፡

 የቫይረስ ሞሎኪውሎች በሰው ሰራሽ እንደ መኪና እና የቤት አየር ማቀዝቀዣ ላይ ተደላድለው ይቆያሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተደላድሎ ለመቆየት እርጥበት እና በተለይ ደግሞ ጨለማ ቦታ ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ የአየር እርጥበታማነትን ማስወገድ፣ ደረቅ፣ ሞቃት እና ብርሃናማ ሁኔታዎችን መፍጠር ቫይረሱ በቶሎ እንዲዳከም ያደረጉታል፡፡

 ማንኛውም ዩቪ ( አልትራቫዮሌት) ብርሃን ያለው ቁስ የቫይረሱን ፕሮቲን ይሰባብረዋል፡፡ ለምሳሌ የአፍንጫ እና አፍ መሸፈኛን አክሞ እንደገና ለመጠቀም ፈጽሞ ውጤታማ ነው፡፡ ነገር ግን ተጠንቀቁ ይህ ብርሃን በቆዳችን ላይ ያሉ የፕሮቲን ክፍሎች በመጉዳት በቆይታ የቆዳ መሸብሸብ እና የቆዳ ካንሰር ሊያስከትል ይችላል፡

 ቫይረሱ ጤነኛ ቆዳ አልፎ ሊገባ አይችልም፡፡ ( ይህማለት ቁስለት ወይም የተከፈተ ቆዳ ካገኝ በቀላሉ ወደ ስውነታችን ሊገባ ይችላ እና መሸፈን እና መጠንቀቅ አለብን ማለት ነው)

 አቼቶ (Vinegar ) የቫይረሱሱን የውጭ ስባማ አካል ሊያሟሟው ስለማይችል ከቫይረሱ ሊከላከል አይችልም

 ማኛውም የመጠጥ አልኮል ወይም በጣም ጠንካራው ቮድካን ጨምሮ ከ40 ፐርሰንት በላይ አልኮል ስለሌላቸው የሚፈለገው 65 ፐርሰንት አልኮል ስለሆነ ከቫይረሱ ሊከላከሉ አይችሉም፡፡

 የአፍ መጉመጥሞጫው የአሜሪካው LISTERINA መጠቀም ከፈለግን 65 ፐርሰንት አልኮል አለው፡፡ ( ጠቃሚ ነው ማለት ነው)
 በተፋፈጉ ጠባብ ቦታዎች እና ክፍሎች ውስጥ ቫይረሱ በብዛት ሊኖር የሚችል ሲሆን በተናፈሱ እና በተፈጥሮ ገላጣ ቦታዎች የቫይረሱ መጠን አነስተኛ ነው፡፡

 ተደጋግሞ ተብሏል ነገርግን እጃችሁን ታጠቡ። አፍንጫችሁን፣ ምግብ፣ የበር መዝጊያዎች፣ እጀታዎች፣ ማብሪያ ማጥፊያዎች፣ የርቀት መቆጣጠሪያዎች፣ የእጅ ስልኮች፣ ሰአት፣ ቴሌ ቪዥን፣ እና መታጠቢያ ቤት ከመጠቀማችሁ በፊት እና በኋላ እጃችሁን መታጠብ አለባችሁ፡፡

 የቫይረሱ ሞሎኪዩሎች በጥቅጥቅ እና ጥቃቅን የእጃችን ሽብሽብ ወይም በተቆረጠ ቆዳችን መሃል ሊቀመጡ ስለሚችሉ በተቻለ መጠን እጃችንን በብዙ ውሃ ማራስ እና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ እጃችንን ባራስነው መጠን የቫይረሱ መጠን በዛው ልክ ይቀንሳል።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

Endalamaw Abera (PHD)

የላቦራቶሪ ምርመራ ነገር
=================
ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር በተያየዘ ተደጋግመው ከሚቀርቡት ጥያቄዎች መካከል “መንግሥት የላቦራቶሪ ምርመራን በስፋት የማያካሂደው ለምንድነው?” የሚለው ይገኝበታል፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠት ቀላል አይደለም፤ ለመጀመር ያህል ግን “ለመሆኑ በእጃችን ያለው የላቦራቶሪ ምርመራ ምን አይነት ነው?” የሚለውን መመለስ ይኖርብናል፡፡ ለዚያ መደላድል እንዲሆን በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎችን በላቦራቶሪ ስለምንለይባቸው የምርመራ አይነቶች መጠነኛ ማብራሪያ ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡

የማቀርበው ጠቅለል ያለ መረጃ ስለሆነ ዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በበቂ ሁኔታ መዳሰስ አልፈለግኩም፡፡ ከላይ እንደገለጽኩት ትኩረቴ በቫይረሶች ላይ ብቻ መሆኑን ተረዱልኝ፤ እሱንም በስፋት ለማቅረብ መሞከር ጠቃሚ ስላልመሰለኝ የተውኩት ብዙ ዝርዝር አለ፡፡ ተጨማሪ መረጃ የሚፈልግ ሰው በውስጥ መስመር ያነጋግረኝ፡፡

1. የሴሮሎጂ ምርመራዎች (Serological Tests)
-------------------------------------------------
እነዚህ የምርመራ አይነቶች የሚለዩት (የሚያገኙት) ሰውነታችን በባዕድ አካሉ (ቫይረስ) ሲወረር የሰጠውን ምላሽ ነው፡፡ ይህም ማለት በአብዛኛው ጸረ-ባዕድ የሆኑትን ፕሮቲኖች (antibodies) መኖር በማረጋገጥ የሚፈጸም ነው፡፡ የቫይረሱ ክፋይ የሆኑ ፕሮቲኖችንም (antigens) መለየት የሚችሉ የመመርመሪያ ስልቶች አሉ፡፡ (ለምሳሌ፤ ለሚለገስ ደም ምርመራ እነዚህን እንጠቀማለን፡፡)

አንዳንዶቹ የመመርመሪያ አይነቶች በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ውጤቱን የሚያሳውቁ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ በሰዓታት የሚቆጠር ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡

ጠቀሜታ
• በተለይም የፈጣን ምርመራ ዘዴዎች የረቀቀ ቴክኒካል ዕውቀትን ስለማይጠይቁ የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎትን እስከ ታችኛው የጤና መዋቅር፡ አልፎ ተርፎም እስከ መኖሪያ ቤት ድረስ ለማውረድ ጥሩ አማራጭ ናቸው፡፡
• በአጭር ጊዜ ብዙ ናሙናዎችን ለመመርመርና የሕክምና ወይም ሌላ ውሳኔ ለመስጠት አመቺ ናቸው፡፡
• ከአንድ ግለሰብ ምርመራ ባለፈ ኅብረተሰቡ ማወቅ ለምንፈልገው በሽታ አምጪ ጀርም ምን ያህል እንደተጋለጠ ለማሳየት ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡
• ከዋጋ አንጻር አብዛኞቹ የፈጣን ምርመራ አማራጮች ውድ አይደሉም፡፡

ችግር
• ሰውነታችን በባዕድ አካላት ከተወረረ በኋላ ተጻራሪ ፕሮቲኖችን እስኪያመርት ድረስ ባለው ጊዜ የምርመራው ውጤት በሽታው መኖሩን አያሳይም፡፡ በኤችአይቪ “Window period” የምንለው ይህንን ነው፡፡ የተጋለጥነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ለሁሉም ጀርሞች ይሠራል፡፡
• በሽተኛው በሕክምናው ከተፈወሰ በኋላም የምርመራው ውጤት ፖዘቲቭ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ የምርመራው ውጤት አተረጓጎም “በሽታው አለበት” ከሚል ወደ “በሽታው ነበረበት ወይም ለበሽታ አምጪው ጀርም ተጋልጦ ነበር” ወደሚል ይቀየራል ማለት ነው፡፡


2. ሞለኵላር ምርመራዎች (Molecular Tests)
-----------------------------------------------------
እነዚህ የመመርመሪያ ቴክኖሎጂዎች የቫይረሱን DNA ወይም RNA በብዙ እጥፍ በማባዛት የሚሠሩ ናቸው፡፡ በቴክኒካል ቋንቋ “Nucleic Acid Amplification Tests (NAAT)” ተብለው ይጠራሉ፡፡ ከነዚህ መካከል በብዛት የሚታወቀው PCR የተባለው የምርመራ አማራጭ ነው፡፡ በኤችአይቪ ሕክምና አገልግሎት ውስጥ የሕክምናውን ውጤታማነት ለመከታተል (ቫይረሱ መድኃኒቶችን የመቋቋም አቅም [resistance] መፍጠር አለመፍጠሩን ለመለየት) የምንጠቀምበት የቫይረስ መጠን (“viral load”) የሚታወቀው በዚህ ምርመራ ነው፡፡ ለጉበት ቫይረሶች ሕክምናም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

ጠቀሜታ
• እነዚህ መመርመሪያዎች የሚለዩት ቫይረሱ ራሱ መኖሩን ስለሆነ በበሽታው የተያዘ ሰው ኔጌቲቭ ውጤት የማሳየት እድሉ እጅግ የመነመነ ነው፡፡
• የሌሎች የመመርመሪያ ዘዴዎችን አስተማማኝነት ለመፈተሽ ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡
ችግር
• የመሣሪያዎቹ (ማሽኖቹ) እና የሌሎች ግብዓቶች ዋጋ ከፍተኛ በመሆኑ በስፋት አልተሰራጩም፡፡
• መሣሪያዎቹን በብቃት ለመጠቀም በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል ያስፈልጋል፡፡
• አንድ መሣሪያ በሙሉ ኃይሉ ቢሠራ እንኳ በአንድ ቀን ውስጥ ሊመረምር የሚችለው ናሙና መጠን የተወሰነ በመሆኑ በቀን ውስጥ ብዙ ሺህ ምርመራ ማድረግ በሚያስፈልግበት ወቅት አዳጋች ያደርገዋል፡፡ (ይህን ችግር ለማቃለል የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እየተሞከሩ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ለእኛ እስኪደርሱን ግን ጊዜ መውሰዱ አይቀርም፡፡)

የኮሮና ምርመራ
-------------------
አሁን ያለው የኮሮና ምርመራ ስልት PCR ነው፡፡ ይህ መመርመሪያ በአፋጣኝ ገበያ ላይ ሊወጣ የቻለው የቻይና መንግሥት የቫይረሱን Sequence በቶሎ ይፋ በማድረጉ ነበር፡፡ ያ መረጃ ከተገኘ በኋላ በርካታ ድርጅቶች የመመርመሪያውን ቅመም አምርተው ለገበያ አቅርበዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅትም ለበርካታ አገሮች ያሰራጨው በዚህ መንገድ ካመረቱ ታዋቂ ኩባንያዎች የገዛውን ነበር፡፡

በአገራችን ውስጥ የPCR መሣሪያ ያለባቸው የተወሰኑ ላቦራቶሪዎች አሉ፡፡ ካልተሰሳትኩ ከአንዱ በስተቀር ሁሉም በማዕከልና በክልል የጤና ምርምር ላቦራቶሪዎች ውስጥ ነው የሚገኙት፡፡ ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ ኮሮናን መመርመር እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡ ይህ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ አንድ ወሳኝ ተግባር በመሆኑ ለጤና ሚኒስቴር አድናቆትና ምስጋና ማቅረብ ይገባናል፡፡

የተለያዩ አገሮች ሴሮሎጂካል መመርመሪያዎችን ለማምረት እየሞከሩ እንደሆነ ይታወቃል፤ መጠቀም የጀመሩ አገሮችም እንዳሉ ሰምተናል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ኖሯቸው በስፋት ሥራ ላይ እስኪውሉ ግን የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል ብዬ እገምታለሁ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ እነዚህ መመርመሪያዎች ወጪ ለመቀነስ ሊያግዙ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፡፡

ተንብይ ብባል… ሩቅ ባልሆነ ጊዜ በርካታ ሕዝብ በሴሮለጂ ከተመረመረ በኋላ ፖዚቲቭ የሆኑትን ብቻ በPCR የምንመረምርበት የሥራ ሂደት (Algorithm) ሊመጣ ይችላል፡፡ በተለመደው የእኛ አነጋገር ሴሮሎጂ መፈተሻ (screening test) ፡ PCR ማረጋገጫ (confirmatory test) ሊሆን ይችላል ማለት ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ.. ከላይ እንዳልኩት ታሞ የዳነ ሰውም በሴሮሎጂ ፖዚቲቭ ሊሆን ይችላል፤ ቫይረሱን በራሱ የመከላከል አቅም ከአካሉ ያስወገደ ሰው ግን በPCR ኔጌቲቭ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የሕክምና ክትትል የሚያስፈልገው በሁለቱም ምርመራዎች ፖዚቲቭ የሆነ ሰው ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡

መልካም ቀን!

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

Post Reply