ስለ ኮረና ዝም አንበል

User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

ህወሓት ኣጋጣሚውን ተጠቅማ የፖለቲካ ስልጣኗን ኮንሶሊዴት እያደረገች ነው። ቀርፋፋውን የፌደራል መንግስት መጠበቅ ሳያስፈልጋት፣ ቆራጥ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው። የእንቅስቃሴ ገደብ ኣስቀምጣለች። የቤት መቀመጥ አዋጅ አውጃለች። ጥሩ እርምጃ ነው። ሽማግሌዎቹ ለራሳቸው ህይወትም የሰጉ ይመስለኛል።

አገሪቱ በጠቅላላ እንዲህ ተገዳ ወደ መዘጋት ከማቅናቷ በፊት፣ አዲስ አበባን ብቻ በፍጥነት እንዲዘጉ በተደጋጋሚ መክረን ነበር። ሽባው መንግስት በየሆቴሉና በየአዳራሹ አልጋ በማንጠፍ በሽተኛ እየተጠባበቀ ነው። ከመታመም በፊት መጠንቀቅ፣ በተለይ ለቫይረስ ደግሞ ከትርጉም አልባ ትሪትመንት ይልቅ፣ ፕረቨንሽን ኣይሻልም ነበር?

ፌደራል መንግስት ሲዘናጋ ክልሎች የራሳቸውን ቁርጠኛ ውሳኔ ይወስዳሉ፣ ልክ እንደ ትግራይ። ለማዕከላዊው መንግስት መዳከምና ለክልል መንግስታት መጠናከር ይህ የራሱ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል። ከበሽታው ብኋላ በተዳከመ አቅም ማዕከላዊ መንግስት ፈተናው ቀላል አይሆንም። የመገንጠልና የመፍረስ አደጋዎች ክፊታችን ናቸው።
User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

"ኮረና የተገኘባቸው እስካሁን 12 ብቻ ናቸው።"

ቫይረሱ የሚሰራጨው exponentially መሆኑ እየታወቀ ከአስር ቀን በላይ ያስቆጠረው በሽታ ዛሬ ድረስ አስራ ሁለት ሰው ላይ ብቻ ተገድቦ ቆማል የሚል የመንግስት ማስተባበያ ህዝቡን ማደንዘዣ ከመውጋትና ከለየለት የወንበዴ ዲስ ኢንፎርሜሽን ዘመቻ ተለይቶ አይታይም።

ቴስት የማድረግና የበሽታውን ስርጭት የመከታተል ኣቅማችን ዝቅተኛ ነው፣ እስካሁን የምናውቀው አስራሁለት ሰዎችን ብቻ ቢሆንም ሌሎች የተጠቁ አይኖርም ማለት አንችልም፣ የሚል ማስተካከያ ነበር በትንሹ የሚጠበቀው።

የፌደራል መንግስት ህዝቡን እያዘናጋው ነው።

ኮረና ኢትዮጵያ ሲደርስ የሚንቀረፈፍበት ምክንያት አይኖርም። በአስር ቀን ውስጥ ሌሎች አገራት በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ላይ ቫይረሱ ተዛምቷል። በኢትዮጵያም ውስጥ ለውስጥ እየተቀጣጠለ ነው። መዘናጋቱ ለማንም አይጠቅምም።
User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

እርግጥ ነው ሽብር መፍጠር ለምንም አይጠቅምም። ባዶ ተስፋ በሚሰጡ አማላይ ቃላት በሽታውን አቅልሎ ማየት ደግሞ የከፋ ነው። ሪያሊስቲክ መሆን ያስፈልጋል። ዜጎች እውነታውን ማወቅ አለባቸው። የችግሩን ጥልቀት መረዳት አለባቸው። ለዚህ ደግሞ የሁሉም ንቃትና ርብርብ ይጠይቃል።

መጀመሪያ ላይ ኮረና አዛውንቶችንና ሌላ በሽታ ያላቸውን (የሰውነታቸው የመከላከል አቅም የተዳከመ) የማህበረሰብ ክፍል ብቻ ነው ለከፋ ችግር የሚያጋልጠው ቢባልም፣ ዛሬ ምንም በሽታ ያልነበራቸው ህጻናትና ወጣቶችም መሞታቸውን እየሰማን ነው። ይህ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ መጀመሪያ ከገመትነውና ከፈራነው በላይ ከባድ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ላስቦካችሁ አይደለም። እንድትጠነቀቁ ነው። ዝለቁና አንብቡኝ።

እንበልና የህክምና ተቋማቱ ማስተናገድ የሚችሉት በቀን 50 ታማሚ ብቻ ነው። በሽታው እየተስፋፋ ሲሔድ ወደ ተቋማቱ የሚጎርፈው በቀን 200 ታማሚ ነው እንበል። ሃምሳውን ለማዳን ሲረባረቡ 150 ትርፍ ከመጣ፣ በማግስቱ ትላንት መታከም ከነበረባቸው ሃምሳ ሲያክሙ ሌላ ተጨማሪ 200 በሽተኛ ከመጣ፣ ወዘተ የሚፈጠረው ቀውስ ቀውስ እንዳይመስላችሁ።
  • የመዳን ተስፋ የነበራቸው አረጋውያንና ሌላ በሽታ የነበራቸው ሰዎች ይሞታሉ።
  • የህክምና ባለሞያዎች ባይሞቱም፣ በተጨናነቀ ሁኔታ የሰው ህይወት ለማዳን ሲረባረቡ፣ በጥንቃቄ ጉድለት (በስራ ጫና ብዛት) ለበሽታው ሊጋለጡና የመስራት አቅማቸው ሊዳከም ይችላል። ከሆነ የህክምና ተቋሙ በፊት መቀበል የሚችለው ሃምሳ ሰው እንኳን መቀበል አይችልም ማለት ነው። ታማሚው ደግሞ አሁንም 200 ምናልባትም ከዛ በላይ በየቀኑ እየጎረፈ ነው። ይህ የለየለት ቀውስ ነው።
  • መሞት የማይገባቸው ወጣቶችና የህክምና ባለሞያዎች ይሞታሉ።
  • በሽተኛው በዚህ ሁኔታ እየተከማቸና ቁጥሩ እየጨመረ ሲሔድ፣ የበሽታው ስርጭት በዛው ልክ ይሰፋል። መሞት ቀርቶ መታመም ያልነበረባቸው ሰዎች ይሞታሉ። ጤነኛ የነበሩ፣ ህጻናት፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና ጎልማሶች ሳይቀር።
  • በኛ አገር ሁኔታ ስታስታምም፣ ስትቀብር፣ ለቅሶ ስትደርስ፣ ምን ስትል፣ የሚተርፍ ሰው አይኖርም።
  • ይህ ሁሉ ሲደማመር ማህበረሰባዊ ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል። ሰዉ ለበሽታው ቀርቶ ለሞት ደንታ አይሰጠውም። ራስን የማጥፋት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።
ወዘተ።

እናም ነገ እዛ ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን እንዳናገኘው፣ ዛሬ አርፈን ቤታችን እንቀመጥ። ንጽህናችንን እንጠብቅ። ሶሻል ዲስታንሲንግ ተግባራዊ እናድርግ። ወዘተ። በጤና ባለሞያዎች የሚሰጡትን ምክር እየተከታተልን ተግባራዊ እናድርግ።
User avatar

Topic author
gebetaforum
Site Admin
Posts: 71
Joined: Fri Aug 18, 2017 12:12 am
Contact:

በዚህ ፍጥነት ከቀጠለ፣ የኮረና ስርጭት በአሜሪካ በዚህ ሳምንት መጨረሻ 300ሺ ይደርሳል ብዬ እገምታለሁ። ዛሬ ከ164ሺ በላይ ነው። እስከ ዛሬ ከ3ሺ በላይ ሰዎች ሞተዋል። ከበለጸጉት አገራት መካከል፣ ኮረና የከፋ ችግር የሚያስከትለው በአሜሪካ ነው።

አንደኛ የሀብት ልዩነቱ የትየሌለ ነው። ሀብታም ገንዘቡን ከሚያጣና ከሚከስር፣ አዛውንትና የጤና ችግር ያለባቸው ቢሞቱ ይመርጣል። ስለሆነም በቂ ኢንቨስትመንት አያደርጉም። መንግስት ኮረናን ለመዋጋት ከመደበው መልቲ ቢልዮን ዶላር በጀት የአንበሳውን ድርሻ የወሰዱት ልክ እንደ 2008 ፋይናንሺያል ክራይስሱ ግዜ ኮርፖሬሽኖችና ባለሀብቶች ናቸው።

ሁለተኛ ቀድሞዉኑ ሄልዝ ኬር ሲስተሙ የወረደ ነው። ከአውሮፓ አንጻር ሲታይ። ስንቱ ድሃ ሄልዝ ኢንሹራንስ የሌለው፣ ለተራ በሽታ እንኳን እንኳን ራሱን ቤቱ አስታምሞ የሚያገግም ነው ያለው። ዛሬ እስኪጠናባቸው ድረስ ዝም ማለት ብቻ ይሆናል እጣፈንታቸው። ይሔ ደግሞ ለበሽታው መዛመት የራሱን ትልቅ ድርሻ ይጫወታል። የመትረፍ እድላቸውም በዛው ልክ ፈተና ውስጥ የገባ ነው።

ሶስተኛ የአመጋገብ ባህላቸው አሜሪካውያን አስፈሪ ናቸው። በስኳር፣ በደም ግፊት፣ በኦቤሲቲ፣ በአስማ በምኑ የተጠቃ፣ ድራግ አዲክትድ ምናምኑ መዓት ነው። እነዚህ በዚህ በሽታ ለከፋ ጉዳት የተጋለጡ ናቸው። የጎዳና ተዳዳሪዎችን ፓርኪንግ ሎት ላይ እያሰመሩ ሶሻል ዲስታንሲንግ ተግባራዊ ለማድረግ ሲሞክሩ የሚያሳይ ፎቶ እዚህ ሰፈር አይቼ ገርሞኛል በጣም።

አራተኛ ፖፕሌሽን ስትራክቸሩን ካየነው አዛውንቶች በጣም ብዙ ናቸው። ለዚህ በሽታ ከተጋለጡ በህይወት የመትረፍ እድላቸው አነስተኛ ነው።

አምስተኛ ማህበራዊ ግንኙነቱና ሶሻል ኔትዎርኩ ኢንተንሲቭ ነው። ስቴት ከስቴት፣ ከተማ ከከተማ፣ ወዘተ ዝውውሩ ከሌሎች አንጻር ሲታይ በጣም ኢንተንሲቭ ነው። ይህ ቀድሞ ከመዘጋቱ በፊት በሽታው በእያንዳንዱ ከተማና ስቴት በስፋት እንዲዛመት ቁልፍ ምክንያት ነው። ከ6 ቀናት በፊት 50 ሺ ገደማ የነበረ ዛሬ ከመቶሺ በላይ ጨምሮ የምናየው ለዚህ ይመስለኛል።

እነዚህንና መሰል ፋክተሮችን ስናይ አሜሪካ የከፋ ችግር እንደሚገጥማት መገመት ይቻላል። እዛ የምትኖሩ ወገኖች ለየት ያለ ጥንቃቄ ማድረግ ሳያስፈልጋችሁ አልቀረም።
User avatar

yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

ኮረና አፕዴት

እስክዛሬ ኮረና ከተገኘባቸው 43 ሰዎች መካከል፣ 64%ቱ በቀጥታ ከውጭ የመጡ ናቸው። 23% የሚሆኑት ከነዚህ ጋር የታወቀ ግኑኝነት የነበራቸው ሰዎች ናቸው። የተቀሩት 13% ገሚሱ የስራቸው ሁኔታ ከውጭ ሰዎች ጋር የሚያገናኝ፣ ገሚሱ ደግሞ በሽታው ከማን እንደተላለፈባቸው በደንብ የማይታወቁ በማጣራት ላይ ያሉ ናቸው። ባጠቃላይ በሽታው ከተገኘባቸው መካከል 30%ቱ ከዱባይ የመጡ ናቸው። አንድ ሶስተኛ ማለት ነው።

ከተያዙት መካከል 70% ወንዶች ሲሆኑ፣ ከ25 እስከ 54 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ደግሞ 80% ናቸው። ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ 13. 5% ገደማ ናቸው። በሽታው ከተገኘባቸው መካከል ከአዲስ አበባ ውጭ የሆኑት 16% ብቻ ናቸው።

የታማሚዎች የእድሜ ስርጭት ስናይ ሌላ ችግር ከሌለባቸው በስተቀር መትረፍ የሚችል እድሜ ላይ ያሉት ያመዝናሉ። በዛ ላይ በአብዛኛው በአዲስ አበበ የተወሰነ ነው።

ይህም ማለት፣ ከውጭ የሚመጡት (በተለይ ከዱባይ የሚመጡት ) ላይ ጥብቅ ኳራንቲን ቢደረግ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ፣ ከድሬዳዋና ባህርዳር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እገዳ ቢጣልባቸው፣ የዚህን በሽታ ስርጭት በጣም ማዘግየት ይቻላል። አንዳንድ ክልሎች ከቀበሌ ወደ ቀበሌ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሳይቀር መገደብ ጀምረዋል። በፌደራል ደረጃ ከትላልቅ ከተሞችና ከውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በጥብቅ ካልታገዱ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው የሚሆነው። በዚህ መንገድ ስርጭቱን ለመግታት አሁንም አልረፈደም።

በፖሊሲ ደረጃ የሚወሰዱ እርምጃዎች ግዜ ለመግዛት ከጠቀሙን፣ የሆነ ሰዓት ላይ ክትባት ወይም ሌላ ዘዴ ሲገኝ ከእልቂት ልንተርፍ እንችላለን። ብሎም በቂ ቁሳቁስና የባለሞያ ዝግጅት እስኪጠናከር ድረስ ግዜ ለመግዛት ያስችላል።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

በኮረና መሃል ትላንት አንድ ጥሩ ዜና ሰምተን ነበር። ይኸውም የ85 ዓመት አዛውንት ማገገማቸው ነበር። ዛሬ 61እና 56 ዕድሜያቸው ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። ያሳዝናል። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ሁለተኛው ሟች ምንም የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና ከውጭ ከመጣ ሰው ጋር ግኑኝነት ያልነበራቸው ናቸው። በበሽታው መያዛቸው የታወቀ እለት እንዴት እንደተያዙ እየተጣራ ነበር። ፕሮግረሱን ስላልተከታተልኩት አላውቅም። (ወይም ፕሮግረስ የለውም ይሆናል።) ይህ የበሽታው ሁኔታ አንድ ደረጃ ከፍ ማለቱን የሚያመላክት ነው። ፈረንጆች ኒው ፌዝ ይሉታል። ሽብር አያስፈልግም። ነገር ግን እውነታውን ማወቅ ተገቢ ነው። ከምንም በላይ በእንቅስቃሴ ገደብ የበሽታውን ስርጭት መቀነስ እንዳለብን ፌደራል ላይ የተቀመጡ ሰዎች ሊያሰምሩበት ይገባል።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

28 ሚልዮን ህዝብ በወረርሽኙ (በኮረና) ሊያዙ እንደሚችሉ የመንግስት የአደጋ ዝግጁነት ሰነድ አመላከተ ይላል ዋዜማ ራድዮ። ባለፈው አንስተነው ነበር። እንደሚመስለኝ በይፋ ለህዝቡ ያላሳወቁት ፓኒክ እንዳይፈጠር ነው። ባለፈው ኮሜንት ላይ ጽፌው የነበረውን የኔን መረዳት አካፈልኳችሁ።

ሁሉም ቦታ ላይ ያለው ግምት ከ50 እስከ 70% በቫይረሱ መያዙ አይቀርም የሚል ነው። በሄርድ ኢምዩኒቲ እንኳን አንድ ማህበረሰብ በሽታውን መቋቋም የሚችለው እስከ ሁለትሶስተኛው ታምሞ እምዩኑን ያሳደገ እንደሆን ነው ይባላል። እናም ቫክሲን ወይም ሌላ መላ ካልተገኘ በስተቀር እስከሚቀጥሉት ሁለት አመታት ቢያንስ ከ50 ሚልዮን ህዝብ በላይ መታመሙ አይቀርም። አሁን ያለው ትልቁ ስጋት የብሽታው ባህሪ በደንብ ባልታወቀበት፣ ህዝቡ ግንዛቤ ባልጨበጠበት፣ መንግስትና የህክምና ባለሞያዎች ባልተዘጋጁትበት፣ በአንዴ ብዙ ሰው እንዳይታመምና መዳን እየቻለ እንኳን በህክምና እጦት ብዙ ሰው እንዳይሞት ነው። እነ ጣልያን ዘንድ ያየነው ይኼንኑ ነው። በዛ አስጨናቂ ሁኔታ ከአቅማቸው በላይ በሽተኞችን ለመርዳት ሲረባረቡ ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው መስዋእት የሆኑ፣ አገሪቱ አንጡራ ሀብቷን ከስክሳ ያስተማረቻቸው ዶክተሮች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ይህንን መሰል ቀውስ ኢትዮጵያ መቋቋም የምትችልበት አቅም የላትም። እናም ዋናው ችግር፣ በአንዴ ብዙ ሰው የሚታመምበት ሁኔታን ማወቅና መቀነስ ነው እንጂ፣ ሰዉ መታመሙ አይቀሬ ነው። አትደናገጡ።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

Post Reply