ስለ ኮረና ዝም አንበል

User avatar

yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

peak.jpg
peak.jpg (70.4 KiB) Viewed 6820 times
.
ይቺን ተዓምረኛ ግራፍ ተመልከቷት። መድሀኒት የለሹ ኮረና፣ የዓለም ሃያላን አገራትን፣ ፊልም ላይ አክተራቸው የማይሞተው፣ ሁሉንም የሚያሸነፉትን ጭምር፣ ዕጣ ፈንታቸው በዚች ግራፍ ብቻ እንድትወሰን አድርጓል። ሌላ አማራጭ የለም። ግራፉ የሚያመላክተው የሚታመመው ሰው ብዛት ከግዜ አንጻር ነው። እየጨመረ፣ እየጨመረ ሄዶ የሆነ ሰዓት ላይ ፒኩ ላይ ይደርሳል። ይቆለላል። ምንም እርምጃ ካልተወሰደ ብዙ ሰው በአጭር ግዜ ይታመማል፣ ቶሎ ፒኩ ላይ ይደርሳል፣ ፒኩ ደግሞ የትየሌለ ነው። ይህ በመንግስት፣ ሎጂስቲክ አቅርቦትና በህክምና ባለሞያዎች የሚፈጥረው ጫና (burden ) ከፍተኛ በመሆኑ የሚሞተው ሰውም በዛው ልክ ይሆናል። የሚሞተው ብዛት በሚልዮኖች ይገመታል። በአሜሪካ ከ2ሚልዮን በላይ ተግምቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ ቀድሞ እርምጃ ከተወሰደ፣ የበሽታውን ስርጭት በማዘግየትና በመቀነስ፣ አንድም ቶሎ ፒኩ ጋ እንዳይደርስ፣ ሁለቱም ስርጭቱን በማራዘም ፒኩን ማሳጠር ይቻላል። ማለትም በአንድ ግዜ ብዙ ሰው ከሚታመም ይልቅ፣ በየጊዜው ትንሽ ትንሽ ሰው እንዲታመም ማድረግ ይቻላል ማለት ነው። ፒኩ (ጫፉ) ሲቀንስ በርደኑ (ጫናው) ይቀንሳል። ጫናው ሲቀንስ፣ የሎጂስቲክ አቅርቦት የተሻለ ይሆናል፣ ባለሞያዎችም ጫናቸው ስለሚቀንስ ብዙ ሰው ማትረፍ ይችላል። ስለሆነም የሚሞተው ሰው ቁጥር ይቀንሳል። አሜሪካ አሁን እየወሰደች ባለችው እርምጃ፣ የሚሞተው ሰው ብዛት እስከ ሁለት መቶሺ ድረስ ተገምቷል።

የሟቹን ቁጥር ከዚህም በታች ማውረድ ይቻላል። ነገር ግን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ይጠይቃል። አሁን በተወሰደው ቤዚክ እርምጃ አሜሪካ የ3 አመት የሚገመት ኢኮኖሚዋን ታጣለች። ማለትም ከበሽታው በፊት ወደነበረው የኢኮኖሚ ማማ ለመመለስ በትንሹ ሶስት አመት ይጠይቃታል።

ኮረና የሰው ህይወት ዋጋው ስንት ነው የሚለውን ከባድ የሞራል ጥያቄ እንድንጋፈጥ አስገድዶናል። የምንወስደው እርምጃ ኢኮኖሚክ ኮስቱንና ህዩማን ኮስቱን ያጣጣመ መሆን አለበት። ለምሳሌ አሜሪካ የሟቹን ቁጥር ከዛ በታች ለማውረድ ኢኮኖሚውን የባሰ ከጎዱት፣ እሱም ራሱን የቻለ ችግር ይፈጥራል። በስራ ማጣት፣ በድህነትና በሌላ ምክንያት ሊሞት ከሚችለው በተጨማሪ፣ ራሱን የሚያጠፋው ሰው ብዛት ቁጥርም ሊጨምር ይችላል። ለዚህ ነው፣ ራይት ባላንሱን መጠበቅ የሚያስፈልገው።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

!*!

የፋሲካ በዓል እየደረሰ ነው። በዓሉን በተለመደው መንገድ የማክበር ሁኔታ የሚኖር አይመስለኝም። ሆኖም ትንሽ ተፍተፍ የሚልም አይጠፋም። ታድያ ሰዉ ከመቼውም ግዜ በላይ ጥንቃቄ እንዳይለየው ዛሬ ማሳሰብ አሰፈላጊ ነው። ለዚህም ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ፡

አንደኛ የመንግስት የመመርመር አቅም ውሱንና ባብዛኛው ከውጭ የሚመጡ ሰዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ነው። የጤና ባለሞያዎች እስካሁን ኮቪድ ያለባቸውን ሰዎች ያወቁት በብዛት ከውጭ የመጡና በኳራንታይን የቆዩ ናቸው። ከዛ ቀጥሎ ከነሱ ጋር የታወቀ ንኪኪ የነበራቸው ሰዎች ናቸው። የመንግስት የምርመራ አቅም የተገደበው፣ ፖቴንሺያል ፖዘቲቭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰበውን ከውጭ የመጡና ከነሱ ጋር ግኑኝነት የነበራቸው ላይ ነው። ከዛ ውጭ ያሉትንና በህዝቡ መሀል ምልክቱን ሳያሳዩ ሊኖሩ የሚችሉ ሰዎችን ማወቅ የሚችልበት አጋጣሚ የለም። በሽታው ጸንቶባቸው ራሳቸው ወደ ህክምና ተቋማት ካልሔዱ በስተቀር ለማወቅ አስቸጋሪ ነው።

ሁለተኛ በራሳቸው ግዜ ወደ ህክምና ተቋማት ሔደው በሽታው እየተገኘባቸው ያሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ዛሬ ሪፖርት ከተደረጉት 3 ሰዎች መካከል ሁለቱ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያልነበራቸው፣ በኮቪድ መያዙ ከታወቀ ግለሰብም ንኪኪ ያልነበራቸው መሆኑን ተዘግቧል። እስከዛሬ ከሞቱት 3 ሰዎች መካከል እንዲሁ ሁለቱ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያልነበራቸውና በኮቪድ መያዙ ከታወቀ ግለሰብ ጋር የታወቀ ግኑኝነት ያልነበራቸው መሆኑ ይታወቃል። ይህም ማለት በቫይረሱ ሊያዙ የቻሉት፣ በህክምና ባልሞያዎች ያልታወቀና በህዝቡ መሃል ኖርማል ህይወታቸውን እየገፉ ካሉ፣ ምልክቱን ያላሳዩ በሽተኞች ነው ማለት ነው።

እናም ይህንን ግምት ውስጥ አስገብተን በጥንቃቄ እንንቀሳቀስ።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe


dan
Posts: 20
Joined: Mon Apr 13, 2020 11:52 pm

የማነ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋን ጨምሮ 14 ሰዎች ድነዋል። በሽታውን የመቋቋም አቅማችን ከፈረንጆች የተሻለ መሆኑን አያመላክትም ትላለህ?
Post Reply