Yaman's ቤት

ECONOMICS, POLITICAL SCIENCE, SOCIOLOGY, ...


Post Reply
User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ነበርኩ ድሮ። ከዛ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ ከምበል አልኩ። በሁለቱ መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። የተማርኩት ዋንኛ ቁምነገር ቢኖር እውነት በተፈጥሮ ሳይንስና እውነት በማህበራዊ ሳይንስ አራምባና ቆቦ መሆናቸውን ነው።

ለምሳሌ ጫካ ውስጥ ሰው በሌለበት አንድ ዛፍ ቢወድቅ ድምፅ ይፈጥራል ወይስ አይፈጥርም ለሚለው የቆየ እንቆቅልሽ፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ያለ ጥርጥር አዎ ሲሉ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለት ይክፈላሉ። ነገሮች በራሳቸው ጊዜ የሉም፣ በኛ ምናብ ውስጥ ብቻ ነው የሚኖሩት ብለው የሚያምኑ የሚወድቀው ዛፍ ሰው ካልሰማው በስተቀር ድምፅ ፈጠረ ማለት አይቻልም ብለው ይከራከራሉ። በአንፃሩ ደግሞ ሰው ኖረም አልኖረ፣ አወቃቸውም አላወቃቸው፣ ነገሮች በራሳቸው ጊዜ ይኖራሉ፣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች አዎን ዛፉ ሲወድቅ ድምፅ ፈጥሯል ብለው ይመልሳሉ።ከዚህ አንፃር ሲታይ ለምሳሌ አዲስ ንጥረ ነገር አገኘን ሲባል ሰዉ ያወቀበት ጊዜ እንጂ ነገርዬው ያኔ ተከስቶ አይደለም። ነገርዬው ነበር ሰዉ ግን አያውቀውም ነበር።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ዛፉ ድምፅ እንደሚፈጥር ያለ ጥርጥር የሚመልሰው እንዴት ነው? ይህን ለመመለስ ድምፅ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ መመስለስ ያስፈልጋል። ወደ አማርኛ መመለስ ይከብደኛል ድምፅ is a vibration that typically propagates as an audible wave of pressure ይለዋል የፊዝክስ መዝገበ ቃላት። የኛ አእምሮ ሞገዱን ( waveን) ኢንተርፕሬት የማድረግ ችሎታ ስላለው ድምፁን እኛ በምንረዳው መልኩ እንሰማዋለን። እኔ ኖርኩም አልኖርኩም ዛፉ ሲወድቅ ያንን ሞገድ ይፈጥራል። ያንን ሞገድ መተርጎም የሚችል ፍጥረት በአካባቢው ካለ "ይሰማዋል" ከሌለ ሞገዱ ከመፈጠሩ የሚያግደው ነገር የለም።

ይህ ምን ማለት ነው በተፈጥሮ ሳይንስ there is objective truth! በተፈጥሮ ህግጋት የሚገለፅ፣ ከህግጋቱ የማያፈነግጥ እውነታ ሁሌም አለ። ድምፁን አልሰማሁትምና ድምፅ አልተፈጠረም ብለህ ሙጭጭ አትልም። ያንተ ምስክርነት በዚህ ግዙፍ ዩኒቨርስ ምንም ናት።

በአንፃሩ ደግሞ በማህበራዊ ሳይንስ ውበት እንደተመልካቹ ነው እንደምንለው ሁሉ እውነት እንደ ሰዉ ይቀያየራል። አንድ ቡድን የፈለገውን እውነታ ፈጥሮ ሊሟዘዝ ይችላል። ታሪክ በአሸናፊዎች ነው የሚፃፈው ወዘተ የምንለው ያለ ምክንያት አይደለም። ፈላስፋው ፎኩልት ፖወር ኢዝ ትሩዝ ሲል ቅልብጭ አድርጎ አስቀምጦታል። ስልጣኑ ያላቸው (የገንዘብ፣ የፖለቲካ፣ የሚሊታሪ ወዘተ ስልጣን ያላቸው) ሰዎች እውነትን በራሳቸው መረዳትና ቁመና ልክ ይፈጥሩታል። የራሳቸውን ጥቅም በሚያራምዱበትና በሚያስጠብቁበት መልኩ እውነታዎችን ይፈጥራሉ። እውነታቸው በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ባያገኝ እንኳን ቢያንስ ቢያንስ ውዥንብር ይፈጥራል።

በማህበራዊ ሳይንስ ይህ ክፍተት በደንብ ስለሚታወቅ በፖለቲካው መስክ የተሰማሩ ሰዎች ዓለምንና ህዝቧን የሚገልፁት በናሬቶቮች ነው። ናሬቲቮች ደግሞ ከርዕዮተዓለም፣ ከግል ግንዛቤና ጥቅም ወዘተ የሚጨለፉ ናቸው። ቢያንስ ከነዚህ ተፅእኖ ነፃ ነው ማለት አይቻለንም። ዛፉ ሲወድቅ ድምፅ ስለመፍጠሩ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ ከሆነ ዛፉ ስለመውደቁም እንድትጠራጠሩ የሚያደርግ ናሬቲቭ ሊያግቷችሁ ይችላሉ።

የኢኮኖሚክስ ተማሪነቴን በጣም የምወደው ይህን የመሰለ የውዥንብር ፈተናን የሚጋፈጥና በዳበሩ የስታቲስቲክናየኢኮኖሜትሪክስ ዘዴዎች እውነታዎችን የማጥራት ስራ በትጥልቀት ስለሚሰራ ነው። የኔ እይታ በኢኮኖሚክስ ቦታ የላትም። ምን ያህሉ ሰው እይታዬን ይጋራል ብቻ ሳይሆን እይታው በራሱ ትክክል የመሆን ዕድሉስ ምን ያህል ነው ብሎ የማጣራት ስራ ይሰራል። (በርግጥ ይህን ዘዴ ማስተር ለማድረግ ጊዜ ጉልበትና ትዕግስት ይጠይቃል። ከባድ ነው።

በአንፃሩ ደግሞ አንዳንድ ሲዶሳይንስ ሊባሉ የሚገባቸው የትምህርት መስኮች አሉ፣ በሳይንስ ስም የማህበራዊ ሳይንስ ውስጥ ተሰግስገው ቀልድ አይሉት ምን ሲቸክቹ የሚውሉ። አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ።

አንዲት የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ነኝ የምትል ሰው፣ ዶክትሬቷን በኢትኖግራፊ ትሰራለች። መመረቂያ ፅሁፏ የሚያጠነጥነው በግሏ ታሪክ ነው። ግሩም ባዮግራፊ ይወጣው ነበር። በደርግ ጊዜ ስለደረሰባት በደል ትተርካለች። እያንዳንዱን ምዕራፍ በራሷ ታሪክ ላይ የተመሰረት ትርክት ጀምራ በራሷ ወይም በምታውቃቸው የሰፈር ሰዎች ገጠመን ትርክት ትቋጫላቸው። እነዚህ ትርክቶች ናቸው እንግዲህ ናሬቲኝቭ ሆነው ጊዜውን፣ ሁኔታውን፣ ስርዓቱን እንደሚገልፁ እውነታዎች በነሱ ዘንድ የሚታዩት። ፈረንጅ ምን ግዱ ነው፣ አስመርቆ ወደ ሰፈሯ ላካት። ዛሬ የጭቆና ትርክት ነፍስ የዘራው በዚህ መንገድ ነው፣ ለማለት ያህል ነው።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

Hidden Content
This board requires you to be registered and logged-in to view hidden content.

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

Post Reply