GMO በዘረ-መል ለውጥ የተደረገባቸው ዘሮች

PHYSICAL AND LIFE SCIENCES


Post Reply
User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

ግልፅ ደብዳቤ
ከዶ/ር ተወልደብርሃን ገብረ እግዚአብሔር
ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም.

ስሜ ተወልደብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ይባላል። በየካቲት 12/2012 ዓ.ም. ሰማንያ ዓመት ሞልቶኛል።

በብሪታንያ ሃገር ሰሜናዊ ዌልስ ውስጥ በሚገኘው ባንጎር ዩኒቨርሲቲ ነው የእፅዋት ስነምህዳር (ፕላንት ኤኮሎጂ)ን በዶክትሬት ትምህርቴን ያጠናሁት።
ከዚህ ችሎታዬ በመነሳት ነው በሃገሬ መዲና በአዲስ አበባ የፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ሥራ ኣስኪያጅ በመሆን ሃገሬን ያገለገልኩት። ጥናትና ምርምሬን በጠቀስኩት ስነ ህይወት ዙሪያ በማድረጌም ነው የደህንነተ ህይወትን እና የዘረመል ምህንድስናን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ድርድሮችን ለማድረግ የኢትጵያን ልዑካን ስመራ የነበረው።

በደህንነተ ህይወት ላይ የተካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ድርድሮች በውጤታቸው ልውጥ ህያዋን በማህበረሰብ፣ በኢኮኖሚና በአካባቢ ላይ የሚያደርሱዋቸውን ተፅንዖዎች የፈተሹ ነበሩ። ይህ ፍተሻ የእፀዋትም ሆኑ የእንስሳት ልውጥ ህያዋን ሊያመጡ የሚችሉዋቸውን አዲስና የማይጠበቁ ኣከባቢያዊ አደጋዎችን መርምሯል። ፍተሻው በዘረመል ምህንድስና ዘሮች ወደ ሌሎች ህያዋን የሚሸጋገሩበትን ሁኔታ እንዲሁም የተፈጠሩት ልውጥ ህያዋን ሊያመጡ የሚችሉትን መዘዝ በአንክሮ ተመልክቶአል።

በዘረ መል ምህንድስና ልውጥ ህያዋንን የመፍጠር ሂደቱ በተለየ ጥብቅ ከባቢ የሚካሄድ ቢሆንና ሊያመጣ የሚችለውም ተፅዕኖ በደንብ ተጠንቶ ለየትኞቹም ህያዋን ጉዳት የማያመጣ መሆኑ ቢረጋገጥ ኖሮ ልውጥ ህያዋንን በመፍጠር ሂደት ሊኖር ስለሚችለው መዘዝ መነጋገሩ በቀረልን ነበር። ልውጥ ህያዋኑም ለሰውም ሆነ ለእንስሳት እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት ይውሉ ዘንድ ፈቃድ ይሰጣቸውም ነበር።

የካርታኼና የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል ብዝሃ ህይወትን የሚጠብቅ ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው። ዓላማውም በዘመናዊ ዘረ መል ምህንድስና የሚሰሩት ልውጥ ህያዋን ጉዳት በማያመጣ መልኩ በጥንቃቄ እንዲያዙ፣ እንዲጓጓዙና በጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ነው።

ይህም በብዝሃ ህይወት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳይኖር ከመከላከሉ ባሻገር የሰው ልጅ ጤናንም ያረጋግጣል። እስከ ዛሬ ድረስ ኢትዮጵያን ጨምሮ የዓለማችን 172 ሀገራት የካርታኼናን የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል አፅድቀውታል።

የካርታኼና የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል በልውጥ ህያዋን የሚጠቀሙ አመራረቶች በተፈጥሮ የሚበቅሉ አዝርዕትንም ሆነ የተፈጥሮን ስርዓት ይዘው የሚራቡ የቤትና የዱር እንስሳትን፥ እንዲሁም ሌሎች የእርሻ መንገዶችን እንዳይበክል ጥንቃቄ ይደረግ ዘንድ መስፈርት አስቀምጦአል።

የካርታኼናው ፕሮቶኮል በተጨማሪም በዘረመል ምህንድስና በተፈበረኩ ምርቶች እሽግ ላይ ልውጥ ህያዋን መሆናቸውን የሚያመለክት ማስታወቂያ መለጥፍ እንደሚያስፈልግ፤ ያም በተፈጥሮ በሚበቅሉና በሚራቡ ምርቶች ብቻ መጠቀምን ለሚፈልጉቱ ምርጫ ሊሰጣቸው እንደሚችል ያትታል።

ይህም መሰረታዊ የማህበራዊ መብት ነው። ማን ምን ማብቀል እንደሚፈልግ፣ ምን መብላት እንደሚፈልግ፣ ምን መልበስና ከተፈጥሮአዊ ከባቢ ጋር ምንአይነት ግንኙነት ሊኖረው እንደሚፈልግ የመምረጥ መብት ነው።

ልውጥ ህያዋን ወደ ከባቢው አንድ ጊዜ ከገቡ እና በከባቢው ውስጥ የሚኖሩትን ህይወቶች ከለወጡ በኋላ ሁሉን ነገር መልሰን በተፈጥሮ ወደ ነበረበት መመለስ ከቶውኑ አይቻለንም። በመሆኑም መሠረታዊ የመምረጥ መብትን ጨርሶ ይሰርዘዋል።

[በተለያዩ ጊዜአትና ቦታዎች] የደህንነተ ህይወትን በተመለከተ የተደራደሩ የኢትዮጵያ ልዑካንን መርቻለሁ። ድርድሩ ሲጀመር የአፍሪካ የተደራዳሪዎች ቡድን አባላት እኔን ዋነኛ ተደራዳሪያቸው እንድሆን መረጡኝ። ያንን ተከትሎም የአዳጊ ሀገሮች የተደራዳሪዎች ቡድን ቀዳሚ ተደራዳሪያቸው አደረጉኝ።

በመጨረሻም ራሱን የማያሚ ቡድን ብሎ ከሚጠራው ስብስብ በቀር ሁሉም የዓለም ተደራዳሪዎች ዋና ተደራዳሪያቸው እንድሆን ጠየቁኝ። የማያሚ ቡድን አሜሪካን፣ ካናዳን፣ አርጀንቲናን፣ ቺሊን እና ኡሩጓይን የያዘ ቡድን ነው።

ድርድሩ ኮሎምቢያ ውስጥ በምትገኘው ካርታኼና በተባለች ከተማ ውስጥ ተጠናቀቀ። እናም በደህንነተ ህይወት ላይ ስምምነት የተደረሰበት ሰነድ የካርታኼና የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል ተሰኘ።

አሁን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት በኢትዮጵያ ልውጥ ህያዋን የሆኑ አዝርዕቶች እንዲመረቱ መፍቀዱን በዜና አነበብሁ፥ ሰማሁ።

ብዙ ነገሮች ያሳስቡኛል። ከሚያሳስቡኝ ነገሮች መካከልም 130 ሄክታር የሚሸፍነው የዘረ መል ጥናት በሌሎች አጎራባች ከባቢዎች ላይ አደጋ የማይደቅን ጥብቅ እርሻ የመሆን ያለመሆኑ ጉዳይ እና እነዚህ ጉዳዮች የደህንነተ ህይወትን ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮል ባማከለ ሁኔታ እንዴት እየተሄደባቸው ነው የሚሉት ይገኙባቸዋል። ፕሮቶኮሉ በሀገራችንም የፀደቀና ዝርዝር አሠራሮቹም በኢትዮጵያ የደህንነተ ህይወት ማዕቀፍ በአካባቢ ጉዳዮች፥ በደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ሕግ፥ ፖሊሲና መስፈርቶች የካቲት 2011 ዓ.ም. የተቀረፀለት ነው።

እነዚህ የሕግ ሂደቶች ካልተተገበሩ አሁን በሚደረገው የልውጥ ህያዋን ምርት ዙሪያ እጃቸውን ያስገቡት አካላት የካቲት 2011 ዓ.ም. የወጣውን ፕሮቶኮል እና በአዋጅ ቁጥር 655/2009 በነጋሪት ጋዜጣ ወጥቶ በቁጥር 896/2015 የተሻሻለውን ሕግ እየተላለፉ ነው።

ይህም ኢትዮጵያ ይፋዊ ባልሆነ ሁኔታ ከካርታኼናው የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል ራስዋን እንዳገለለች ሊያስቆጥራት ይችላል። እኔ እስከማውቀው እስከአሁን ድረስ ኢትዮጵያ ሕግጋቱን ጠብቃ ቆይታለች፤ አስፈላጊ ሆና ባገኘችውም ጊዜ ሕጎችዋን አሻሽላለች እንጂ በይፋ ከካርቴሄናው የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል አልወጣችም። ጡረተኛ እንደመሆኔና 80 ዓመት እንዳለፈው አንድ አረጋዊ ከኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት ጋር የቀጥታ ግንኙነት የለኝም። ስለሆነም ኢትዮጵያ የካርቴሄናውን የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮልን ሕጋዊ ትግበራ ገሸሽ እያደረገችው ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጉዳይ የማጣራበት መንገድ የለኝም።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት የካርታኼናውን የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል ሕጋዊ ትግበራ ገሸሽ እያደረገው ከሆነ፤ ሀገሪቱ ዓለምአቀፍ ስምምነትን እየጣሰች መሆኑ ግልፅ ይሆናል።

ይህ እንዲሆን ሊፈቀድለት አይገባም። እናም የትውልዱ ወጣቶች በሚችሉት መንገድ ሁሉ ተቃውሟቸውን ያሰሙ ዘንድ አሳስባለሁ። ይህን የምልበት ምክንያትም የካርታኼናውን የደህንነተ ህይወት ስምምነት ጨምሮ የፀደቁትን ዓለምአቀፋዊ ሕጎች በይፋ ወጥቼባቸዋለሁ ሳይሉ መጣስ በመሆኑ ነው። በሀገራችንም ሆነ በአፍሪካ አህጉር ብሎም የማያሚ ቡድን ከሚባለውና አምስት ሀገራትን ብቻ ካቀፈው ተቃዋሚ ቡድን በቀር በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የሕጋዊነት መሰረት ማናጋትም በመሆኑ ነው።

በመጨረሻም የየሀገራቸው መንግስታት የደህንነተ ህይወት ስምምነቶችን ጨምሮ ዓለምአቀፍ ሕግጋትን በዓለም ዙሪያ አክብረው መተግበራቸውን እንዲቀጥሉ ይወተውቱ ዘንድ፤ የአፍሪካን እና የቀሪውን ዓለም ወጣቶች አበክሬ አሳስባለሁ።

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

An open letter by Dr. Tewolde Berhan Gebre Egziabher

My name is Tewolde Berhan Gebre Egziabher. I turned 80 on 19 February 2020.

I studied in Bangor, North Wales, United Kingdom, for my PhD in plant ecology. It is obvious that there is an overlap between plant ecology and animal ecology.

It is with this background that I served my country as the Director-General of the Environmental Protection Authority of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, based in Addis Ababa, my country’s capital. It was because of this background that I led the Ethiopian delegation, including in the negotiations on biosafety and genetic engineering.

The outcome of the global negotiations on biosafety included the full socio-economic and environmental impact assessment of genetically modified organisms. This assessment looks at possible new and unexpected outcomes of plants and animals that could be harmful to the environment. It includes the transfer of genes modified through genetic engineering to life forms and their possible consequences. This can be avoided if it is done in a contained environment and as and when the effects have been studied and are found to be safe for all forms of life, the genetically modified organism will be allowed for use as food, feed as well as for industrialization. The Cartagena Protocol on Biosafety to the Convention on Biological Diversity is an international agreement which aims to ensure the safe handling, transport and use of genetically modified organisms (GMO’s) resulting from modern biotechnology. This will prevent adverse effects on biological diversity, taking also into account risks to human health. To date, 172 counties around the globe, including Ethiopia, have ratified the Cartagena Protocol on Biosafety. The Cartagena Protocol on Biosafety also requires that the cultivation of genetically modified organisms does not pollute organic agricultural crops and animals, wildlife, and other farming practices that must avoid contamination by the modified gene in the area where they are growing. It also includes the appropriateness of labelling genetically modified organisms to inform those who wish to use non-genetically modified products so that they are assured of their choice. This is a fundamental social right, the right to choose what to grow, what to eat, what to wear, and how to interact with the environment. Once a modified gene gets into the environment and the living organisms therein it cannot be taken out, eliminating the right to choose.

I led the Ethiopian delegation in the negotiations in biosafety. When the negotiations started, the African Group of Negotiators chose me to become their chief negotiator. Following that, the Developing Countries Group of Negotiators asked me to be their lead negotiator. Finally, all the negotiators except those who called themselves the Miami Group also asked me to be their chief negotiator. The Miami Group consisted of the United States of America, Canada, and Argentina, Chile, and Uruguay. The negotiations were finalized in Cartagena, which is a city in Columbia. Thus, the final agreed biosafety protocol is called the Cartagena Protocol on Biosafety.

Now, I read and heard in the news that the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia is allowing the cultivation of genetically modified crops in Ethiopia. I have several worries, including the feasibility of 130,000 hectares of research being a contained environment, and how these things have been legally handled with the biosafety protocol as it stands ratified and procedures defined by the Biosafety Framework of Ethiopia defined by the Law, Policy, and Standards of the Directorate General of the Environment, Forest and Climate Change Commission, in February 2019. If these have not been implemented, the involved parties are breaking the law, stipulated in February 2019 and laws gazetted in Proclamation No 655/2009 that was amended in 896/2015. It would also mean that Ethiopia has de-facto withdrawn from the Cartagena Protocol on Biosafety. To the extent that I know, Ethiopia has thus far kept all its laws and replaced or amended them when necessary, and it has not legally withdrawn from the Cartagena Protocol on Biosafety. As a retired old man past 80 years of age, I have no direct contact with the Federal Government of Ethiopia. Therefore, I have no way of checking whether Ethiopia is simply ignoring the legal status of the Cartagena Protocol on Biosafety or not.

If the Federal Government is simply ignoring the legal status of the Cartagena Protocol on Biosafety, then it would be obvious that it is breaking international law. This should not be allowed to happen. Therefore, I want to encourage the younger generation of Ethiopians to protest in all the ways they can. This is because breaking an international law, which includes the Cartagena Protocol on Biosafety, without legally withdrawing from it, is breaking international law and degrading rule by law in Ethiopia, in the continent of Africa and in the world at large with the exception of the members of the Miami Group, which are only 5 countries as opposed to the rest of the globe.

I would also urge the young generations of Africa and the rest of the world to urge their respective governments to continue respecting international law, including biosafety, globally.

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

እምቢ ለGMO!
Solomon Negash

አብይ አሕመድ በዚህ ግርግር ጊዜ በፓርላማ እንዲጸድቅ ያደረገውን GMO የሚደግፉ ሰዎች ስለ ግብርና ምንም አይነት እውቀት የሌላቸው ናቸው። የቴስላ መኪና ሲያስተዋውቅ የሚውል ነው GMOን የስልጣኔ ምልክት አድርጎ ወስዶ ሲያበቃ ያላንዳች እውቀት አፉን ሞልቶ የሚናገረው። ዳሩ ምን ያደርጋል፣ በእጽዋት ሳይንስ፣ በአካባቢ ሳይንስ፣ በብዝሀ ህይወት ወዘተ ፒኤችዲ የያዙ ሰዎች ሞያቸውን ትተው የብሔር ፖለቲካ ነው ሲፈተፍቱ የሚውሉት። ይህ ይመስለኛል ለማንም "ዘመናይ" ነኝ ባል በር የከፈተው። እንጂ እንኳን በፓርላማ ለማጽደቅና ለመከራከር፣ መታሰቡስ?

ምን ስለሆነ ነው GMO እንድንቀበል የተደረገው? ግብርናችን ኋላቀር ነው ከተባለም፣ ኋላቀር ያደረገውን አሰራር መቀየር አይቀልም? ገበሬው ከሚያመርተው በላይ በቢሮክራሲ ትብታብና በሙስና ባለስልጣኖቹ የሚዘርፉትና አገሪቱን የሚያከስሯት አይበልጥም? በሙስና የሚጠፋው የአገር ሀብት፣ ግብርናውን ለማዘመን ቢውል የስንቱን ህይወት መቀየር በቻለ ነበር። ለምሳሌ እንውሰድ፣ መሬት ለትላልቅ የውጭ አገር ኢንቨስተሮችና መሪዎች ብርካሽ ዋጋ ከመቸብቸብ ይልቅ፣ ለስራ አጡ ወጣት ቢታደልና እነ ሜቴክ ያባከኑት ብር፣ ለወጣቱ የብድር አገልግሎት ቢውል፣ እርሻው በዘመነ፣ ምርት ባደገ፣ የትና የት በተደረሰ ነበር።

ያ ብቻ አይደለም፣ እነ ጉና ከውጭ የሚያስመጡት ማዳበሪያ፣ ትርፍ ላይ ብቻ ያተኮረ ነው። የኢትዮጵያ የግብርና ባለሞያዎች መች እንደትልቅ አጀንዳ ይዘው ለመቀየር እንደሚታገሉ ባላውቅም ያለው አሰራር ትክክል እንዳልሆነ ሁሉም ያውቃል። ማዳበሪያ የሚቀርበው በብላንኬት ሪኮመንዴሽን ነው። ይህም ማለት፣ ሁሉም አይነት አፈር ላይ፣ ሁሉም አይነት የአየር ጸባይ ላይ፣ ሁሉም አይነት አካባቢ ላይ (ውሃ ገብና ደረቅ ወዘተ)፣ ለአንድ የሰብል አይነት ሪኮመንድ የሚደረገው የማዳበሪያ መጠን ተመሳሳይ ነው። ይህ ስህተት ነው። ወጪና ኪሳራው የት የሌለ ነው። መሬቱን በማበላሸት ረገድም የራሱ ችግር አለው። ሁሉም ያውቃል። ያንን ለማስተካከል ግን ሲሞክሩ አይተን አናውቅም። ማዳበሪያ በማያስፈልገው መሬት ጭምር ማዳበሪያ ሸጦ ጊዜያዊ ትርፍ ለመቀራመት ነው ሩጫው። ማዳበሪያው አገር ቤት የሚመረት ቢሆን ደግሞ ባልከፋ፣ ነገር ግን ሁሉም እንደሚያውቀው ከውጭ ነው የሚገዛው። ገበሬው የትርፍ ምንጭ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ጤናው ላይ ሊያስከትል የሚችለው ችግርም አለ። ለረዥም ጊዜ ከተጠቀመ ደግሞ መሬቱን ያለማዳበሪያ ማልማት አይችልም። ይህም በደንብ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ከቁብ የቆጠረው ባለሞያ ያለ አይመስለኝም። በተለይ ስልጣን ላይ የሚወጡት፣ ሪፎርም እናደርጋለን የሚሉት፣ የአገሪቱን የአየር ጸባይ፣ የኑሮ ዘይቤ፣ የግብርና ባህልና እውቀት ወዘተ ላይ መሰረት ያደረገ ሪፎርም ሲሞክሩ አይተን አናውቅም። ፊሊፒንስ ይህን አድርጋ ተለውጣለች እንሞክረው፣ ህንድ ይህን አድርጋለች እንሞክረ፣ ቬትናም ይህን አድርጋለች እንሞክረው። ይኸው ነው የነበረው አሰራር። አሁንም ያለው። እነዚህ አገራት በአየር ጸባያቸው፣ በግብርና ባህላቸው፣ ወዘተ በሁሉም ነባራዊ ሁኔታዎች ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል አይደለም። ኮፒ ፔስት እዚህ ላይ አይሰራም።

ከGMO የሚገኝ ትርፍ ምን እንደሆነ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም። አየር ላይ አይበቅል። ያለስራ እንደ አረም ራሱን ችሎ አይበቅል። ልክ እንደሌላው አዝርዕት ስራና እንክብካቤ ይጠይቃል። ሌላውም አገር በቀሉ ዝርያ፣ ከሰራህበት ይሸልማል። ያውም ጤናማ ምግብ። ገበሬው ተግቶ እንዲሰራ፣ በሰራው ልክ እንዲያገኝ፣ የተለያዩ ኢንሰንቲሾችን መቅረጽ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ የብድር አቅርቦት፣ የምርት ግብአት አቅርቦት፣ ከተቻለም ሰብሲዳይዝ ማድረግ ወዘተ። ከሁሉም በላይ ደግሞ የመንግስት ትልቁ ስራ ገበያውን መከታተል ነው። ገበሬው ተቸግሮና ለፍቶ ካመረተ ብኋላ ጤናማ ባልሆነ የገበያ ጨዋታ ነው ሁሌም የሚከስረው። ለምሳሌ እንውሰድ። እርዳታ በሚያስፈልግበት የክረምት ወቅት የካናዳና የአሜሪካ ስንዴ ድራሻቸው የለም። ያኔ ጎተራ ውስጥ ተቆልፎባቸው እየነቀዙ ነው። ገበሬው ምርቱን አፍሶ ለገበያ ሲያደርስ፣ ታህሳስና ጥር ላይ የነቀዘ ስንዴያቸው በእርዳታ መልክ ተራግፎ፣ ገበያውን ያንኮታኩተዋል። የእርዳታ ስንዴ በገፍ ሲቀርብ፣ ስንዴ ብቻ አይደለም የሚረክሰው። ለምግብ ፍጆታ በስንዴ ሊተኩ የሚችሉ ሰብሎች በጠቅላላ ይረክሳል። እናም ገበሬ በዛን አመት ስንዴ አመረተ ገብስ ወይም ማሽላና በቀሎ ዋጋ የለውም፣ መክሰሩ አይቀርም። ገበሬው ምርቱ በዚህ መልክ ዋጋየለሽ ሲሆን ለሚቀጥለው አመት በርትቶ እንዳይሰራ ይገፋፋል። በሌሎች ነገሮች ላይ በተለይ በእርዳታ ተለጣፊ እንዲሆን ያደርጋል። ያ ብቻ አይደለም። ዛሬ በሁሉም አካባቢ የምታዩት በእርዳታ አማካኝነት የመጣ ለአገሩ እንግዳ የሆነ የአረም ወረርሽኝ ኢኮኖሚያችንና የገበሬውን ህይወት በብዙ መልኩ ጎድቶታል። እነዚህንና የመሳሰሉ ለኋላቀርነት ምክንያት የሆኑ አሰራሮችና ፖሊሲዎችን ሳይቀይር፣ በገበሬውና በተፈጥሮ እያሳበቡ GMOን ካልተቀበልን ማለት የድንቁርና ጥግ ነው።

እነሱ ለGMO ብቻ አይደለም ለሌላም እያዘጋጁን ነው። ለነሱ 110 ሚልዮን ህዝብ፣ ህዝብና አገር ሳይሆን ኮንስዩመር ነው። ሸማች። የሀብት ምንጭ። የአንድ ግዜ ሸማች ሳይሆን ቋሚ ሸማች እና ዲፐንደንት እንድንሆን ለማድረግ በአንድም በሌላም መንገድ ሲያመቻቹን ኖረዋል። እኛ ዛሬም ድረስ አልገባንም። የራሳችንን ጤፍ አስፈጭተው ለገበያ በማቅረብ ሮያሊቲ ፐይመንት እንዲሰበስቡ ድጋፍ ያደረገ የመንግስት ተቋም ነው እንግዲህ ዛሬም GMOን ካልተቀበልን ሞተን እንገኛለን የሚሉት።

እንዴት ዝም ይባላል? እምቢ በል! በቃ!

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

A renowned geneticist and agronomist cautions against the adoption of GMO crops
Ethiopia Observer

A renowned Ethiopian geneticist and agronomist has cautioned against the adoption of a genetically modified (GM) variety, saying that it could pose a serious threat to the tremendous genetic and biological diversity of the country. Dr. Melaku Worede, a plant geneticist and former Director of the Ethiopian Plant Genetic Resources Centre, said that any move to improve the agricultural inputs of the country should take into account the interests and desires of local farmers who have been maintaining and adapting their indigenous crop resources for centuries, and should not be imposed in a top-down fashion, he said in an interview with TechTalk With Solomon, a weekly technology TV show on Ethiopian Broadcasting Service (EBS).

Melaku, 84, said that the preservation of indigenous seed varieties which he said are not only cost-effective for farmers but was the most sustainable way to develop agriculture should be an utmost priority. “Attempts to improve agricultural outputs should be done in collaboration with farmers, not by imposing it upon them. Let us explore the genes that we have on the ground first and make good use of it. Knowledge system and the material go hand in hand, he said.

“It is too risky to rely on seeds that have no local adaptation and built-in genetic diversity. Farmers should rather be helped to improve the genetic performance of crops than to be dictated to buy costly GM seeds. In the context it is being developed and used, GMOs has a danger. It is a double-edged sword. “Let us be careful not to be a basket case,” he told the interviewer. “From the farmer’s point view, the yield was not the only criterion, farmers place also importance to diversity in seasons, topography, taste, specific harvest that could be used for specific cultural activities, and a number of things. For farmers, sustainability is an important criterion. They have developed the strategy to spread the risk between factors of season, location, and diversity. So their varieties will have enough plasticity to allow them to grow in diverse conditions.” he said.

Though many are voicing their concern about the risk of smallholder’s loss of sovereign control of their seeds as western companies push to enhance their access to Ethiopian markets, the Ethiopian government is showing a willingness to accept the uptake of GM seeds. In a recent meeting, the Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR) Director, Tadesse Daba said that Bt-cotton was permitted for a confined field trial in 2016 and licensed in 2018, the first for the country. GM maize is also currently under confined field trial to check whether it really prevents diseases or not, he said.

Dr. Melaku said Bt-cotton could be Trojan Horse for the acceptance of other genetically modified crops. “If we partner with profit-generating multinational corporations, it would have enormous implications for our food supply. And the corporations are using Bt cotton as an entry point and they would go on to introduce more GM crops. And they are saying say trial. Where do they conduct the trial? When you do that in a crowded place, there is a potential risk of toxicity,” he said.

“We need technology. We need novel techniques. I am not against the technology per se”, said Melaku, who has built himself an international reputation for preserving the country’s genetic wealth by building the seed conservation center in the country. “We have other types of farming methods that are delivering drought-tolerant crops and enhancement value.

“Can we adopt GM technology here? It could be done in uniform topographic such as Canada and the US prairies, he said, adding, “but here in a country like Ethiopia, in a small-scale farming area that does not even cover one kilometer and the character of the soil and air varies, it would be practically impossible,” he said.

Born in 1936, Melaku Worede obtained a Ph.D. in Agronomy (Genetics and Breeding) from the University of Nebraska, USA in the 1960s. He returned to Ethiopia and became involved in the planning of the Plant Genetic Resources Centre in Addis Ababa, of which he became Director in 1979. He held this post until his retirement in 1993 to join the Seeds of Survival Programme of Ethiopia, which he founded with the support of a consortium of Canadian NGOs led by the Unitarian Service Committee (USC/Canada). He was awarded the Right Livelihood Award in 1989 “for preserving Ethiopia’s genetic wealth by building one of the finest seed conservation centers in the world.”

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

User avatar

Topic author
yaman
Posts: 86
Joined: Mon Sep 11, 2017 12:50 pm

የዘረመል ቅይስ አካል (GMOs) ስጋት በኢትዮጵያ
Addis Mekonnen | አዲስዘመን

‹‹Genetically-Modified seed was never intended to support human life, but to eliminate it.›› ግሎባል ሪሰርች ነው ይህን ያለው፡፡ ግርድፍ ትርጉሙ የዘረመል ቀይስ አካል የሰው ልጅን ህይወት ለመደገፍ ሳይሆን ለማጠፋት የተፈጠረ ነው እንደማለት ነው፡፡
የዘረ-መል ልውጥ አካል (GMOs) በሀገራችን ምሁራን ዘንድ ከፍተኛ የመከራከሪያ አጀንዳ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ በተለይ የአሜሪካ የግብርና ተቋም ኢትዮጵያ የዘረ-መል ልውጥ አካልን መቀበሏን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረትን ሰቧል፡፡ ምሁራንም በሁለት ጎራ ተከፍለው ክርክሩን ተያይዘውታል፡፡
ስለ ዘረ-መል ልውጥ አካል (GMOs) ከማውራታችን በፊት ምርታማነትን ለማሳደግ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ ሂደቶችን እንመልከት፡፡

የዝርያ መረጣ
ይህ ሂደት ለአካባቢው፣ ለዓየር ንብረቱና ለአፈሩ የሚስማማ የዘር አይነትን የመምረጥ ሂደት ነው፡፡ ከመደበኛው ዘር ውስጥ ድርቅ፣ ውርጭ ወይም ሌላ የአካባቢ ተፅዕኖን መቋቋም የሚችሉትን እየመረጡ የተሻለ ምርት ሊሰጡ የሚችሉበት ቦታ ማልማትን የሚመለከት ነው፡፡ ለምሳሌ ከተለያየ የበቆሎ ዝርያ ውስጥ የተሻለውን መርጦ እያላመዱ መዝራት ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ በእንስሳትም ላይ ይተገበራል፡፡ ተፈጥሯዊ በመሆኑ አካባቢ ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ አያስከትልም፡፡

ማዳቀል
ሁለት ተመሳሳይ የሖኑ ነገር ግን የተለያየ ምርት የሚሰጡ እፅዋትን ወይም እንስሳትን ማዳቀልን የሚመለከት ነው፡፡ ለምሳሌ የስጋ ጣዕሙ ጥሩ የሖነን የአንድ አካባቢ የበግ ዝርያ መጠኑ ከፍ ከሚል የሌላ አካባቢ ዝርያ ጋር በማዳቀል በጣዕምም በመጠንም የተስተካከል የበግ ዝርያ መፍጠር ይቻላል፡፡ ይህ አሰራር በተለምዶ የአሜሪካን ላም ወይንም የአሜሪካን በሬ በሚል የሚታወቁት ከአበሻ በሬ ወይም ላም ጋር በማዳቀል በወተትም በቁመናም የተሻሻሉ ዝርያዎችን ማውጣት ተችሏል፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ ሂደቱን በጠበቀ መልኩ የሚደረግ የማዳቀል ስራ ነው፡፡ በዘር ደረጃም የበቆሎና የሰንዴ ምርትን በዚህ ሂደት ማሳደግ ተችሏል፡፡ ነገር ግን የመነሻ ዝርያዎቹ እንዳይጠፉ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡

የዘረመል ቅይስ አካል (GMOs)
ይሄኛው ቴክኖሎጂ በጣም ውስብስብና በከፍተኛ ላብራቶሪ ውስጥ የሚተገበር ነው፡፡ ትልቅ እውቀትና ቴክኖሎጂንም ይጠይቃል፡፡ አሰራሩ ተፈጥሯዊ ከሆነ ውጭ የሁለት ተቃራኒ አካላትን (ለምሳሌ የእንስሳትን የዕፅዋት፣ የነፍሳት፣ የሰውን ወዘተ) ዘረ መል በመውሰድ በከፍተኛ ላብራቶሪ ውስጥ በማስገባት አንዱን ዘረ መል ከሌላው ዘረመል ጋር የመቀየስ አሰራር ነው፡፡ በቅየሳውም አዲስ ዝርያን ማውጣት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድን በቆሎ ድርቅ እንዲቋቋምና ከፍተኛ ምርት እንዲሰጥ ከሌላ አካል ለምሳሌ ከአሳ ዘረመል ተወስዶ ይቀየስና አዲስ ዘር ሆኖ ይወጣል፡፡ አጨቃጫቂ የሆነው ጉዳይ ከዚህ ውጤት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ተቃውሞና ድጋፍ ነው፡፡

ይህኛው ቴክኖሎጂ በልተው ለማደር ለሚፍጨረጨሩ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ድሃ ሀገራት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ ድርቅን በመቋቋም አርሶ አደሩ ከፍተኛ ምርት እንዲያገኝ ያስችለዋል፡፡ ካገኘው ምርት ደግሞ ሸጦ ህይወቱን እንዲለዉጥ እና የተሻለ ኑሮ እንዲመራ ይረዳዋል፡፡ የአርሶ አደር መለወጥ ደግሞ የሀገር መለወጥ ነው፡፡ ይህ ከላይ ያለው ጥቅም ነው፡፡ ‹‹ይህንን ቴክኖሎጂ መተግበር አለብን›› ብለው የሚከራከሩ ምሁራን መናገር ወደ ማይፈልጉት ጉዳይ እንግባ፡፡

የእኔ የሚባል ዘር ማጣት
የዘረ-መል ቅየሳ የተደረገላቸው ዘሮች ባለቤታቸው በዘርፉ የተሰማሩ ካምኒዎች ብቻ ናቸው፡፡ ካፓኒዎቹ በከፍተኛ ወጪና በትልቅ ላብራቶሪ ለፈጠሩት አዲስ የተቀየሰ ዘር የባለቤትነት መብት ይወስዳሉ፡፡ ዘሩን ወስዶ የሚዘራ አርሶ አደር ሁሉ ለዚህ ካምፓኒ የባለቤትነት ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለበት ማለት ነው፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በጣም አሳሳቢውና የዘር ቅኝ ግዛት የሚባለው የዘረ መል ቅየሳ የተደረገላቸው ዘሮች መሃን መሆናቸው ነው፡፡ ያ ማለት የዘረመል ቅየሳ የተደረገለት አንድ የባቄላ ዘር ዘንድሮ ቢመረት በቀጣይ አመት ከተመረተው ምርት ላይ ለዘር መጠቀም አይችልም፡፡ ስለማይበቅል፡፡ ምክንያቱም ዘሩ መሃን ስለሆነ፡፡ ዘር ለማይበላ አርሶ አደር ይህ ሞት ነው፡፡ ጎተራው ውስጥ ምርቱን አስቀምጦ ከካምፓኒዎች ዘር እንዲገዛ ማስገደድ ነው፡፡ ዘሩን የሚያቀርቡ ካምፓኒወች ደግሞ በመፃ ገበያ ‹‹ባለፈው አመት ጥሩ ምርት ስላገኘህ ዘሩ ላይ የዋጋ ጭማሪ አደርጌብሃለሁ›› የማለት መብት አለው፡፡ ድርጅቱ ይህንን ቢል ለዚህ አርሶ አደር ማንም ተከላካይ አይኖረውም፡፡ መሄጃም ስለማይኖረው የተባለውን የማድረግ የባርነት አለም ውስጥ ይገባል፡፡ ዞሮ ዞሮ ጫናው መንግስት ላይ ይወድቃል፡፡ ቅይስ ዘሩን በዶላር ከውጭ ለማስገባት እንደኛ ላለች በዶላር ድርቅ በተደጋጋሚ ለምትመታ ሀገር ሌላ ቀውስ መፍጠር ነው፡፡ መሰረቴ ግብርና ነው የሚለው መንግስትም አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል፡፡

ሌላው ከዚሁ የባለቤትነት መብት ማጣት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ በዘረ መል ቀይስ አካል የተዘራ መሬት በቀጣዩ አመት በሚዘራ መሬት ላይ የዘረ መል ውርርስ ማካሄዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዘረ መል ቅይስ አካል ላይ ምርምር የሚያደርግ ተመራማሪ ከምርምር ቦታው ዘሩ አፈትልኮ ወጥቶ ቢገኝ ተመራማሪው ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቀው ደንግጋ የነበረው ለዚህ ነው፡፡ አሁን ምን አዲስ ነገር ተፈጥሮ ወደዚህ ስርዓት እየተንደረደረች እንደሆነ ሊፈተሽ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

ይህ አሰራር ተጠናክሮ በሄደ ቁጥር በብዝሃ ህይወት ሃብት ቀዳሚ የሆነቸው ሀገራችን ሃብቷን ሙሉ ለሙሉ አጥታ በላብራቶሪ የሚመረት ዘር ላይ ጥገኛ ሆና መቅረቷ ነው፡፡ በተለይ ከ80 በመቶ በላይ እፀዋቶቿ ለመድሃኒትነት ጥቅም ላይ ይውላሉ ለሚባልላት ሀገረ- ኢትዮጵያ ነገርዮሹ አሳሳቢ ይሆናል፡፡

በነገራችን ላይ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች እጃቸው በዶላር የረዘመ ነው። እኛ ሀገር እንዲገባ የፈቀዱትና ለጉዳዩ ወግነው የሚከራከሩ ወገኖች ይህንን ችግር ሳይረዱት ቀረተው ነው ተብሎ አይታሰብም። ነገር ግን ድርጅቶቹ በአፍሪካ ውስጥ የዘር መል ቅይስ አካል በህግ ደረጃ እንዲረቀቅና እንዲተገበር የዶላር እጃቸውን መዘርጋታቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች ስላሉ የእኛዎቹን ፈቃጆች አካውንት ፈትሽ ማድረጉ አይከፋም!!

የጤና ጉዳቱ
በዚህ የዘረ መል ቅየሳ ዘዴ የተመረተ ምርት ለካንሰር፣ ለውርጃ፣ ለአዕምሮ እድገት ውስንነት፣ በሽታ የመከላከል አቅምን ማሳጣትና የመሳሰሉን እንደሚያመጣ ከGMO ገለልተኛ የሆኑ ጥናቶች አረጋግጠዋል። ጥናቶቹ እንዲወገዱ በማድረግና አጥኚዎችን እስከማሳደድ የሚደርሱ እርምጃዎች የዘርፉ ካምፓኒዎች እንደሚወስዱ የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ ሰሞኑን ዘ- ጋርዲያን በዚህ ዙሪያ የሰራውን የምርመራ ሪፖርት መመልከት ከበቂ በላይ መረጃ ይሰጣል፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ ይህ አሰራር መተግበር አለበት ብለው የሚከራከሩ ሰዎች በምንመገበው ምግብ ላይ መተግበሩ ጉዳት ያመጣል የሚለው ሃሳብ የሚያይል ከሆነ በጥጥ ላይ ለምን አንጠቀምበትም ብለው ይከራከራሉ፡፡ ይህ መከራከሪያም ውሃ የሚያነሳ አይደለም። የጥጥ ፍሬ ለዘይትነት ያገለገላል። በምግብ ውስጥ ዘይት ስሚገባ በተዘዋዋሪ ለምግብነት ዋለ ማለት ነው። የጥጥ ፍሬው ተጨምቆ ዘይት ከሆነ በኋላ ያለው ውጋጅ ደግሞ ለእንስሳት መኖ ይውላል። ይህንን የተመገቡ እንስሳቶችን ስጋና ወትተ ደግሞ ሰው ይመገባል። በዚህ መሰረት ከላይ ለዘረዘርናቸው በሽታዎች የሚያጋልጡ ሁነቶች ይኖራሉ ማለት ነው፡፡

ጥጥ ለልብስ መስሪያ ያገለግላል። በዚህ ምርት የተሰራውን ልብስ ሰው ይለብሳል። የሰው ልጅ ሰውነት ደግሞ በርካታ ቀዳዳዎች አሉት። የልብሱ ብናኝ በቆዳችን ውስጥ ገብቶ ወደ ሰውነታችን ይገባና ጉዳት ያመጣል።
ንቦች የጥጥ አበባን ይቀስማሉ፡፡ ማር የሰራሉ፡፡ ማሩ የዘር መል ቅይስ አካል ውጤት ሆኖ ይገኛል፡፡ ሰው ይመገባል፡፡ ተዘዋወሪ ጉዳቱ ይህንን ይመስላል፡፡ ይህ ብቻሳይሆን በርካታ አርሶ አደሮቿ ማር አምራች የሆነች ሀገር ማር ወደ ውጭ ልላክ ብትል ገዢ ታጣለች፡፡ በዓለም ገበያ ኦርጋኒክ ማር ብቻ ነው ተፈላጊው፡፡ ይህንን የቢቲ ጥጥ ውጤት የሆነው ማር በዓለም ገበያ ላይ ተፈላጊ አይደለም፡፡ የባሰውኑ ኢትዮጵያ ኦርጋኒክ ማር የላትም በሚል የማር ገበያውን ዘግቶት ያርፋል፡፡
ይህ ከላይ የጠቀስነው በቀጥታ ምግቡን ሳንመገበው በተዘዋዋሪ የሚያደርሰውን ጉዳት ነው። በዚህ መሰረት ቀጥታ ለምግብነት በሚውሉት ላይ የሚደርሱትን ጉዳት መግልፁ ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ በ130 ሄክታር መሬት ላይ ቢቲ የተሰኘ በዘረ መል ቅይስ የተደረገለት ጥጥ መዝራቷን የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት በቅርቡ ለሸገር ተናግሯል፡፡ ይህ የጥጥ ዘር ቅድሚያ ወደ አርሶ አደሩ እንዲሰራጭ የተደረገው ሰው ሰለማይመገበው በጤና ላይ ጉዳት አያመጣም በሚል ነው። ከላይ በጠቀስነው መሰረት አካባቢያዊ ቀውሱን ማስላት ቀላል ነው፡፡

መሬቱ
በዘረ መል ቅይስ አካል አንድ ጊዜ የተዘራበት መሬት በቀጣይ አመት ያንኑ ባህሪ ይወርሳል። ለምሳሌ ዘንድሮ የተለውጠ ጥጥ የተዘራ መሬት ቀጣይ አመት በቆሎ ብንዘራበት መሬቱ የወረሰውን ቅየሳ ለበቆሎው ያጋባበታል። ስለዚህ በቆሎውም የዚያን ባህሪ ይዞ ይወጣል። የቢቲ ጥጥ ባለቤት የእሱን ባህሪ የወረሰውን በቆሎም የባለቤትነት መብት ሊያነሳ ይችላል፡፡ መሬቱም ለፀረ አረምና ፀረተባይ የሚጠቀመው ኬሚካል ለኬሚካሉ ሱሰኛ ሆኖ ያንን ካላገኘ ምንም ነገር አላበቅልም ይላል። የነጠፈ መሬት ታቅፎ ማልቀስ!!

ምርት
የዘረ መል ቅይስ አካል አርሶ አደሮች እጅግ ከፍተኛ ምርት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ የሚታሰበውም ምርታቸውን ሸጠው ተጠቃሚ ይሖናሉ ተብሎ ነው፡፡ ነገር ግን የዘረ መል ቅየሳ የተደረገለት ምርት የአውሮፓ ሀገራትን ጨምሮ ወደ ሀገራቸው እንዳይገባ ያገዱ ሀገራት በርካቶች ናቸው፡፡ የቴክኖሎጂ ዘግይቶ ተጠቃሚነት ጥቅሙ ከሌሎች ኪሳራ ለመማር ነው፡፡ እኛ ሀገር ግን ወደ ጥፋቱ እየተንደረደርን ይመስላል፡፡ በዚህ መሰረት የሚመጣውን ተጓዳኝ የጤና ችግር እንቻለው ቢባል እንኳ በዚህ ዘዴ ሀገራችን በምርት ተትረፍርፋ ወደ ውጭ እንላክ ብንል ማን ነው የሚገዛን? የሚለው ጥያቄ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ምን ፍለጋ ነው ወደዚህ ስርዓት ውስጥ የምንገባው? ምን አይነት አዙሪት ውስጥ ነው እየገባን ያለነው?

መንግስት ለምን ያምታታናል?
የካርታኼና የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል በልውጥ ህያዋን የሚጠቀሙ አመራረቶች በተፈጥሮ የሚበቅሉ አዝርዕትንም ሆነ የተፈጥሮን ስርዓት ይዘው የሚራቡ የቤትና የዱር እንስሳትን፥ እንዲሁም ሌሎች የእርሻ መንገዶችን እንዳይበክል ጥንቃቄ ይደረግ ዘንድ መስፈርት አውጥቷል፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ የካርታኼና የስነ-ህይወታዊ አካባቢ ጥበቃ ስምምነትን ፈራሚ ሀገር ናት፡፡ ዛሬ ህግ ጥሳ የዘረ መል ልውጥ አካልን ወደ ተግባር ለማስገባት እየተንደረደረች ነው፡፡ ቢቢሲ አማርኛ ያናገራቸው በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ምርት ልማት ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ለማ "ኢትዮጵያ በሰፋፊ እርሻዎች በባለሃብቶች ብቻ ለማምረት ሁለት ጂ ኤም ኦ የጥጥ ዝርያዎችን ብትመዘግብም፤ ይህ በጥቅሉ አገሪቱ እነዚህን ምርቶች ተቀብላለች ወደሚል ድምዳሜ መድረስ አይቻልም" ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ "ሁለት ዝርያዎችን ከህንድ አምጥተን ሞክረን፤ ስኬታማ ናቸው ተብሎ በዝርያ ደረጃ ተመዝግበዋል። ሌሎች አገራት እንደሚያደርጉት ለእህል ግን አልፈቀድንምም" ብለዋል፡፡

ለሸገር ሬዲዮ ማብራሪያ የሰጡት በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ምርምር አስተባባሪ ዶ/ር ታደሰ ዳባ ደግሞ በእንሰት እና በበቆሎ ላይ ሙከራ እየተደረገ መሆኑን አልሸሸጉም፡፡ በተለይ በእንሰት ላይ ሙከራ ተደርጎ በሽታን እንደሚቋቋም ታመኖበታል ብለዋል፡፡ ዘገባው 130 ሄክታር መሬት ላይ በዘረ መል ቅይስ አካል ጥጥ ተዘርቶ እየተመረተ ነው ብሏል፡፡ ዶ/ር ዳባም የፓርላማ አባላት ሳይቀሩ ተመልክተውት ፍቃድ አግኝቶ ይህንን የሚቀራረብ መሬት መዘራቱን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ህግ መሰረት እንደዚህ ያሉ የተቀየሱ ዘሮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የታገደ ቢሆንም በቅርቡ የተወሰነ ማሻሻ ተደርጎ ለምርምር ብቻ እንዲገቡ መፈቀዱን ተናግረዋል፡፡ በንግግራቸው ውስጥ ሁለት የተጋጩ ነገሮች ማስተዋል ይቻላል፡፡ መጀመሪያ የተሻሻለው ህግ ለሙከራ ብቻ እንደሚፈቅድ ገልፀው አሶሳ ላይ በዚህ ምልኩ ጥጥ መልማት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ ለምርምር ብቻ የሚለው ህግ ተጥሶ ወደ ምርት ተገብቷል ማለት ነው፡፡ ከህዝብ ተሸሽጎ የሚሰራ ስራ መኖር የለበትም፡፡ ይህ በጣም አሳሳቢ ነገር ነው፡፡
የዘር መል ቅይስ አካል እንዳይተገበር ስትከራከር የነበረች ሀገር፣ በዓለም ላይ አሉ የተባሉ ምሁራኖቿ ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሆን ሲከራከሩ የነበሩ ሰዎች ያሉባት ሀገር በየት በኩል እጇ እንደተጠመዘዘ አልታወቀም፡፡ ይህንን አሰራር በመቃወም ገትራ ይዛ የነበረች ሀገር ዛሬ ስለተንበረከከች የዘርፉ ድርጅቶች ደስተኛ ሆነዋል፡፡ ይህንን በመቃወም የተለያዩ ምሁራን የኢትዮጵያ መንግስትን እያሳሰቡ ይገኛሉ፡፡ (በሹክሹክታ…) እዚህ ጋር ቀስ ብሎ ለጉዳዩ የወገኑ የመንግስት ባለስልጣናትን የዶላር አካውንት መፈተሹ አይከፋም፡፡

የዓለም ተሞክሮ
የቡርኪና ፋሶ አርሶ አደሮች በዚህ መልኩ የተቀየሰ የጥጥ ዘር ዘርተው በርካቶች ለኪሳራ መዳረጋቸው ይነገራል፡፡ ቡርኪናፋሶ ይህንን አሰራር በጥጥ ምርት ላይ ሞክራ ከ2011-2016 ድረስ ብቻ 86 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ ደርሶባታል። ትርፉ ቀርቶ ኪሳራ ውስጥ መዘፈቅንም ጭምር ነው እንደ ሀገር እያሳሰበን ያለው፡፡ በኋላ አርሶ አደሮች በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመውት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አገዳ ጥለውበታል፡፡
አሶሳ ላይ የተዘራው 130 ሄክታር የጥጥ መሬት ለየትኛው ገበያ እንደሚቀርብ አብረን የምናየው ይሆናል፡፡
የህንድ አርሶ አደሮች በዚህ አሰራር እዳ ውስጥ ተዘፍቀው ራሳቸውን እንዲያጠፉ ምክንያት የሆናቸውን፣ የኢትዮጵያ ምሁራን ኢትዮጵያ ውስጥ መተግበር የለበትም ብለው የሚሟገቱለትን ይህንን የዘረ መል ቅይስ አካል መንግስት በምን አይነት መልኩ እንደሚያየው ግልፅ መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

የዘር መል ቅየሳን ያገዱ ሀገራት
በዓለም ላይ 26 ሀገራት ይህንን የዘረ መል ቅይስ አካል አግደውታል። ስዊዘርላንድ፣ ኦስትሪያ፣ አወስትራሊያ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሃንጋሪ፣ ሉግዘንበርግ፣ ቡልጋሪያ፣ ፖላንድ፣ ጣልያን ከነዚህ ውስጥ ይጠቀሳሉ። ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለ እዳ አይቀበለውም ነው ነገሩ፡፡

ለዘረመል ቅይስ አካል ደጋፊዎች
‹‹የዘረመል ቅየስ አካል በኢትዮጵያ መተግበር አለበት›› የሚሉ ወገኖች ጋር በአንድ ጉዳይ ብቻ ስምምነት ላይ መድረስ ይቻል ይሆናል፡፡ ይህም የተለወጠው ዘር ባለቤቶቹ የኢትዮጵያ ካምፓኒዎች ከሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ምርምር ያወጡት ቅይስ አካል ካለ ቢያንስ ባለቤቶቹ ኢትዮጵውያን ናቸውና የተጓዳኝ ጉዳቱን ብንችለው በባለቤትነት እንካሳለን በሚል ነገሩን ማቻቻል ይቻል ይሖናል፡፡ ነገር ግን ከውጭ የመጣን መሃን ዘር ‹‹ተቀበል›› ብሎ መከራከር ለውጭ ካምፓኒዎች ባሪያነት ዜጋን አሳልፎ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡

ማጠቃለያ
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ እጅግ ሃብታም ሀገር ናት። ከዳሉል እስከ ዳሽን፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ዓለም ላይ ያለ ተፈጥሮና የአየር ንብረትን ጠቅልላ ያየዘች ግሩም ሀገር። ይህንን የተመለከቱ ሰዎች ተፈጥሯዊ የሆነውን ዘራችንን እየወሰዱ አንድም እነሱ ከሰሩት ዘር ውጭ ማብቀል እንዳንችል ሁለትም በሰው ልጅ ጤና ላይ አደጋ በመጣል በሰው ሰራሽ ቅይስ ዘር ምክንያት በቁጥጥራቸው ስራ ለማድረግ ተነስተዋል።
ተፈጥሮ በራሷ በሚዛን የተሰራች ናት። ይህ ሚዛናዊነት ሲዛባ ነው የሰው ልጅ ችግር ውስጥ የሚወድቀው። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ እጅግ ሃብታም ሀገር ናት። ሰው ካልታመመ በስተቀር መድሃኒት አይወስድም። ባልታመመበት መድሃኒት ወስዶ በዚያ መድሃኒት ላይ ጥገኛ እንዲህም አይፈልግም። ለገንዘብ ያደሩት በሽታ ፈጥረው መድሃኒት ይሸጡልናል። የመድሃኒታቸው ጥገኛ ያደርጉና ደንበኛቸው አድርገው ገንዘብ ይሰሩብናል። ሊሆን የታቀደው ይህ ነው። በገዛ መሬታችን ላይ ጉድጓድ እየቆፈሩልን ነው።
ይህንን ስንል የመንግስት በምግብ ራስን የመቻል አጣብቂኝና የአርሶ አደሮችን የኑሮ ደረጃ ሳንረዳ ቀርተን ሳይሆን ለልጅ ልጆቻችን የሚተርፍ እዳ ላለማውረስ ስንል ብቻ ነው፡፡

"I have great faith in fools; self-confidence my friends call it." - Edgar Allan Poe

Post Reply