የስብሓት ማስታወሻ
በእግዚአብሔር አምናለሁ … ፓርቲው ደግሞ እግዚአብሔር የለም ይላል … ስለዚህ እኔ ለመንግሥት በመሥራት ማገልገል እንጂ በሃይማኖቴ ምክንያት የፓርቲው አባል ልሆን የተፈቀደልኝ አይደለሁም። ዘነበ ወላ፦ “ጋሼ፣ የማርክስን ፍልስፍና አንብበው የሰው ልጆች አልተረዱትም ወይስ ተግባራዊነቱ ላይ ነው ያልሰመረላቸው?” ስብሐት፦ “ይኸውልህ፣ እንደ ማነኛውም ወንጌል ነው የማርክስ ወንጌል። ለድሆች ደህንነት የቆመ ነው። ከኢየሱስ ወንጌል የሚለየው በአንድ ነገር ብቻ ነው። […]